" አባቴ እግዚአብሄር ይባርክህ " - በቅርቡ በሞት የተለየው የአቶ ሰሎሞን አዲስ ታምሩ የመጨረሻ የስንብት ቃል እና ሽኝት42:57ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛView Podcast SeriesFollow and Subscribe Apple Podcasts YouTube Spotify Download (39.32MB)Download the SBS Audio appAvailable on iOS and Android አቶ ሰሎሞን አዲስ ታምሩ ባደረበት ህመም ሳቢያ ሚያዚያ 22 ቀን 2026 ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል ። አቶ ሰለሞን ወደ አውስትራሊያ ለመጀመሪያ የመጡት የአቶ አዲስ ታምሩ ሁለተኛ ልጅ ሲሆን ፤ እናቱ ወ/ሮ ሊሊያን ኒኮላስ የአቦርጅናል ዝርያ ያላቸው ናቸው። የጸሎት እና ሽኝት ስነ ስርአቱም በደብረ ሰላም መድሃኒአለም ሜልበርን ቤተክርስቲያን ተከናውኗል። ስርአተ ቀብሩም ሰኞ ሜይ 21 ቀን 2026 በሜልበርን ተፈጽሟል። በሽኝት ስነስርአቱ ላይ በሜልበርን እና በአውስትራሊያ የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተዋል ። በስፍራው ከተገኙት መካከልም ፤ መላክ ጸሃይ ቀሲስ መንግስቱ ሀይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አህጉረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የብሪዝበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ : መላከ አርአያም ቀሲስ ተስፋ ኅሩይ - የሜልበርን ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ : አቶ እሸቱ ሙሉጌታ ፤ ወ/ሮ ተኛኜ ወርቅ ብስራት ፤ ጄሰን አዲስ ታምሩ ( ወንድም ) ፤ ታሻ ፊትዝክላረንስ (ሚስት) ወ/ሮ ቅድስት ደስታ ፤ አቶ አበራ አያሌው እና ወ/ሮ ቆንጂት ጥላሁን የተሰማቸው ህዘን ገልጸዋል።አንኳሮችበአውስትራሊያ የመጀመሪያው ሰፋሪ ልጅ እረፍትየልጅነት ጊዜ እና አስትዳደግየሀይማኖት አባቶች የሽኝት መልእክትየማህበረሰቡ አባላት መልእክቶችShareLatest podcast episodesየኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት በተመለከተ በአዲስ አበባ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደርን ጠርቶ አነጋገረ" እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ " - ወ/ሮ እመቤት አሰፋ የቅድስት ማርያም የኢትዮጵያውያን ሴቶች ማህበር በሲድኒጎልጎታ - ለሰዓሊና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ"ለእኔ ገብረክርስቶስ ደስታ በጣም ሀገራዊም፤ ዘመናዊም ነው። በሥራዎቹ ውስጥ የቀረርቶ፣ ፉከራና የቅኔ መንፈስም ይታየኛል" ከበደች ተክለአብ