አንኳሮች
- ከልጅነት እስከ ዕውቀት
- ከወሎ - መቀሌ
- ከመቀሌ - ወሎ
- ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ
- ሕልፈተ ሕይወት
- ዝክረ መታሰቢያ
- ምስጋና
ትሁት፣ ቀናና ለልጆቿ፤ ለባለቤቷ ፍቅርን የምትለግስ ናት። ለእሷ ስላለኝ ፍቅር፤ ለእሷ ያለኝን አክብሮት ለመግለፅ ቃላት ያጥረኛል። እሷ እንደዚያ ናት።የወ/ሮ ወርቅነሽ ጥላሁን ባለቤት አቶ አብርሃም ተዘራ
ወርቅነሽ፤ ትሁት ልጅ ነበረች። ጥሩ ልጅ ነበረች። ለባሏ አሳቢ ነበረች። ከሰው ጋር ተግባቢ፤ ጥሩ ባሕርይ ያላት ነበረች።የወ/ሮ ወርቅነሽ ቤተሰብ የቅርብ ወዳጅ አቶ ፍቅሬ (ራያ) ረታ
እህታችን ወ/ሮ ወርቅነሽ ፀዳለ ማርያም፤ እግዚአብሔርን ፈሪ፣ ቤተክርስቲያን አዘውታሪ፣ በቅዱስ ስጋው፣ በክቡር ደሙ፣ በንስሃ የኖረች፤ እጅግ በጣም ቅን ሰው ነበረች። እግዚአብሔር ዕረፍተ ነፍስ ያድልልን። ለልጆቿ፤ በጥበብ፣ በሞገስ፣ በሃይማኖት ማደግን ያድልልን። ባለቤቷን ያፅናናልን።መልአከ ፅዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ፤ የሜልበርን መካነ ሰላም ልደታ ለማርያም ወገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪና የወ/ሮ ወርቅነሽ የንስሃ አባት





