"ልጄ 'ማሚ እኔ ይኼን ቆዳዬን አልወደምው፤ ቀዪሪልኝ' ሲለኝ የተሰማኝን ስሜት በቃል ለመግለፅ ይከብዳል። በጣም ነው የከፋኝ።" ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ

Gete Negash .png

Gete Negash. Credit: SBS Amharic

ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ፤ በሀገር ቤት ጎሠኝነትን፣ በሀገረ አውስትራሊያ ዘረኝነትን እምቢኝ ያሉ፤ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በእጅጉ የኩራት ሞገስን የተላበሱ ናቸው። ልጃቸው ዕድሜው አምስት ዓመት ሊሞላ ደርሶ ሳለ የገጠመው የቀለም ልዩነት ያሳደረባቸውን ሥነ ልቦናዊ ሁከት እንደምን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ፈውስ ሆኗቸው ከእነ ልጃቸው እንደተቋቋሙት ይናገራሉ። ያም አስባብ ሆኗቸው "አድዋና ሜልበርን" ያሏትን የስንኝ ቋጠሮ ያስደምጣሉ።


አንኳሮች
  • ውልደትና ዕድገት
  • ዘረኝነትና የስሜት መታወክ
  • የኢትዮጵያዊነት ፈዋሽ መንፈስ
  • ሥነ ግጥም "አድዋና ሜልበርን"
  • ማኅበረሰባዊና ሀገራዊ የአንድነት ጥሪ
የሰባተኛ እና ስምንተኛ ክፍል መምህሬ ጋሼ ልዑል ይባላል። ኢትዮጵያዊነቴን ከሠሩት ሰዎች መካከል ትልቁን ቦታ የሚወስደው እሱ ነው። እግዚአብሔር ነፍሱን በገነት ያሳርፍ።
ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ
አውስትራሊያ ውስጥ ጉርብትናው፣ አብሮ የመኖሩ ማኅበራዊ ሕይወት በጣም የተለየ ነው። ተፈልጎ፣ ተደክሞ፣ ተጥሮ፣ ተግሮ ካልሆነ በስተቀር፤ ብቸኝነቱ በጣም የሚያስቸግር ሀገር ነው።
ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ
እንደ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አንድ ላይ ብንሠራ፣ መብታችንንም፤ ግዴታችንንም የምናሳውቅበት መንገድ ብንፈጥር እላለሁኝ።
ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ
ወደፊት ይኼን ፊታችን የተጋረጠውን የዘር፣ የጎሣ ፖለቲካ አውልቀን ጥለን፤ ኢትዮጵያን የውጪው ዓለም እንደሚያያት ታላቅ ብናደርጋት። ለእዚያ ደግሞ ምስጢሩ አንድ መሆን ነው። አያቶቻችን ጣሊያንን ድል የነሱበት ምክንያት አንድነታቸው ነው። ከሚያለያየን ይልቅ፤ አንድ የሚያደርገን ይበልጣል። እሱን አይተን አብረን ወደፊት ብንሔድ።
ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ

Share

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now