አንኳሮች
- የሕፃናት ጤና
- የሬዲዮ 018 እና ሃሊ ሾው የቴሌቪዥን አገልግሎቶች
- የስብዕና ግንባታ ስልጠና
- የመጽሐፍ ሕትመት ዋጋ ንረት
- መጽሐፍ ሻጮችና ደራሲያን
የኢትዮጵያ ሕፃናት በሰላም፣ በጤና ሊያድጉ የሚችሉበት ሁኔታ እያለ፤ ተግዳሮት ውስጥ እንዲገቡ ወይም ሕይወታቸው እስከሚቀጠፍ ድረስ ደርሰናል። ይኼን ለማስቀረት ነበር ቆርጬ የተነሳሁት። ለሀገሬ ለኢትዮጵያ በሕፃናት ዙሪያ ነው ለመሥራት የተፈጠርኩት እስከምል ድረስ።ሃሊ ሙዘይን
በጎ ፈቃደኝነት ስንል፤ አብዛኛው ሰው 'መች እኔን ደልቶኝ' ይላል። በጎ ፈቃደኛ ለመሆን ዋነኛው ሰው መሆን በቂ ነው። በሳምንት ውስጥ አንድ ሰዓት ለበጎ ፈቃድ ማዋል ይቻላል።ሃሊ ሙዘይን
ብዙ ጊዜ አደጋ የሚደርሰው ወይም ሕይወትን የምናጣው ባለ መደማመጣችን ነው። በመደማመጥ መፍትሔ ይገኛል። ሁሉም ሰው ውስጥ መልስ አለ።ሃሊ ሙዘይን
ከ12 ዓመት ጀምሮ ሱስ ውስጥ ያሉ ሕፃናት ያጋጥሙኛል። ለእዚያውም በጣም ከባባድ ከመድኃኒት ጋር የተያያዙ፤ በመርፌና በመዋጥ የሚወሰዱ ናቸው። በጣም ልብ የሚሰብር ሁኔታ ነው ያለው። የሚያሳዝነው ወላጆችን ሳናግር 'ልጄ ጨዋ ነው፤ ምንም አያውቅም' ነው የሚሉት። ልጆቻቸውን አያውቋቸውም።ሃሊ ሙዘይን
መጽሐፍ ሻጮች ስልጠና ቢሰጣቸው ደስ ይለኛል። የሚያስከፋቸው ከሆነ ይቅርታ፤ ዕውነታ ስለሆነ ነው። የማስተዋወቁና የስርጭቱ ሁኔታ የሚያበረታታ አይደለም። ለደራሲያን የሚሰጡት ክብር በጣም አናሳ ነው። በጣት የሚቆጠሩ ጥቂቶች ካልሆኑ በስተቀር። መጽሐፍ ከተረከቡ በኋላ ስልክ እንኳ አይመልሱም። ደራሲ ምን ማለት እንደሆነና አንባቢ ምን ማለት እንደሆነ ስልጠና ተሰጥቷቸው ፈቃድ ያላቸው ሆነው ቢሰማሩ ደስ ይለኛል።ሃሊ ሙዘይን
ሴት ደራሲት መሆን ትልቅ ጠቀሜታ አለው። ዓለምን በሴት ዕይታ አይተን የተለየ፤ ወንዶች ያላዩትን፣ የማያዩትን፣ የማያውቁትን፣ ሊሆንም ይችላል የማይሉት ብዙ ዕይታዎች ስላሉ። እነሱን አይተን መፃፍችን bonus ወይም ጉርሻ ነው የሚሆነው። አስደሳች ነው።ሃሊ ሙዘይን
ደራሲና አርታኢ መሆን፤ ልጅ መውለድና አዋላጅነት ያለው ዓይነት ስሜት ማለት ነው።ሃሊ ሙዘይን





