አንኳሮች
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ትንንሽ ባንኮች ተዋህደው ጠንካራ ተቋም መፍጠር ካልቻሉ በስተቀር ያለውን ውድድር መቋቋም እንደማይችሉ ገለጠ
- ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የሚዘረጋው Eastern Africa Power Integration ፕሮግራም የመጀመሪያ ምዕራፍ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ፕሮጄክት ጋር በተያያዘ ሶስት አማካሪ ኩባንያዎች በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በሚሠሩ ፕሮጄክቶች ላይ እንዳይሳተፉ ለ21 ወራት ዕገዳ ተጣለባቸው
- ለንግድና ቱሪዝም ወደ አሜሪካ የሚገቡ ዜጎቻቸው 15 ሺህ ዶላር ዋስትና እንዲያሲዙ ከሚገደዱ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ተካተተች
- የገንዘብ ሚኒስቴር ኢትዮጵያና ጣሊያን የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታወቀ
- 100 ሺህ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተነገረ
- በኢትዮጵያ በልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ የሚፈቀድላቸው ባንኮች የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት መስጠት ግዴታቸው ነው ተባለ
- በሚቀጥሉት አራት ዓመታት 300 ሚሊዮን ዶላር ብድር አነስተኛ ማሳ ላላቸው ገበሬዎች ሊቀርብ ነው
- ከነዳጅ ሽያጭ አሻጥር ጋር በተያያዘ ከ613 በላይ ሰዎች ታሰሩ





