ጮቄ ኢኮቱሪዝም፤ከተስፋ አስቆራጭ ቢሮክራሲ ፍልሚያ እስከ የዓመቱ ድንቅ የዓለም ቱሪስት መንደር14:26Abiy Alem with his wife and child. Credit: A.Alemኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛView Podcast SeriesFollow and Subscribe Apple Podcasts YouTube Spotify Download (10.34MB)Download the SBS Audio appAvailable on iOS and Android የኢኮቱሪዝም ባለሙያው ዐቢይ ዓለም ከጀርመናዊት ሚስቱ ጋር አገረ ጀርመን ለቅቆ ጎጃም ጮቄ መንደር ተስፋ ሰንቆ የገባው በሙያው የአካባቢውን አርሶ አደሮች ሊያግዝና ለተፈጥሮ ጥበቃም የድርሻውን ሙያዊ አስተዋፅዖ ለማበርከት ነው። ይሁንና የጠበቀው ዕቅፍ አበባ፣ የተዘረጉ እጆች፣ አማትረው የሚያዩ ዓይኖችና ክፍት ልቦች አልነበሩም። ከቶውንም "የመንግሥት ሥራ አስፈፃሚዎች ይስቁብኝ፣ ያንቋሹሽኝ፣ ይጠየፉኝና ሥሩለት ሳይሆን አትሥሩለት ነበር የሚሉት" ሲል በምሬት ያነሳል። መገባደጃው ላይ በደረስነው 2022 የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ከአምስት አኅጉራት፣ 18 አገሮች ውስጥ ከ136 መንደሮች መካከል ነቅሶ 32 መንደሮችን 'ድንቅ የቱሪዝም መንደሮች' ብሎ ሰይሟል። ከኢትዮጵያ የኢኮቱሪዝም ባለሙያው ዐቢይ ዓለም ጮቄ ሙሉ ኢኮቱሪዝም መንደር የዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርን ሞገስ ለመላበስ በቅታለች።አንኳሮችጮቄተስፋ፣ ተግዳሮቶችና የስኬት ጉዞኢኮቱሪዝም ተጨማሪ ያድምጡ"ሕዝብና መንግሥት ከደገፉን ጮቄ ተራራ፣ጉና ተራራና ላሊበላ አቡነ ዮሴፍ እንዲተሳሰሩ ለማድረግ አቅሙና ዕውቀቱ አለን" ዐቢይ ዓለሙShareLatest podcast episodesፕሬዚደንት ትራምፕ በሆርሙዝ ሰርጥ መተላለፊያ ተገትተው ያሉ መርከቦችን በተለያዩ ሀገራት ጥያቄ በእጀባ እንዲያልፉ እንደሚያደርጉ አስታወቁየነዳጅ ዋጋ አቀናነስ ጥቆማዎች | ትኩረት ነዳጅ ላይሀገራዊው የምክክር ጉባኤ ምርጫው እንደተጠናቀቀ ይጀመራል ተባለወደ ጎን የተገፋውታሪክ፤ የአቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴተኞች አገልግሎት በአንዛክ ቀን