ጃኑዋሪ 26 በየዓመቱ ዑደቱን ጠብቆ ብቅ ሲል የአውስትራሊያ ቀን አከባበር ለነባር ዜጎች "የወረራ" እና "የሐዘን" ቀን ሆኖ፤ ለሌች "የአውስትራሊያ ዕለተ ልደት" ተደርጎ በመታየት ብርቱ ክርክሮችን ያስነሳል። የቀድሞው የኒው ሳውዝ ዌይልስ ብላክታውን ፖሊስ መድብለባሕል ማኅበረሰብ አገናኝ መኮንን አሰፋ በቀለ፤ ለበርካታ ዓመታት የታደሙበትን የMyall creek የጅምላ ግድያ ዝክረ መታሰቢያና የይቅርታ ሥነ ሥርዓትን ከአውስትራሊያ ቀን ፋይዳ ጋር አሰናስለው ይናገራሉ።
Share






