አቶ በሪሁን ደጉ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር እና የዳያስፖራ ጉዳዮች ክፍል ሃላፊ

.

Ato Bryihun Degu Source: SBS Amharic

“ ክብርት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም መንግስት ባጸደቀላቸው መሰረት ያለደሞዘ እና ያለ ኢምባሴው ውክለና እስክ መስከረም 30 ድረስ በእረፍት ላይ ይቆያሉ ። ‘’


አቶ በሪሁን ደጉ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር እና የዳያስፖራ ጉዳዮች ክፍል ሃላፊ በቅርቡ ከስራቸው በእረፍት ላይ ባሉት በተሰናባቿ ክብርት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም  ዙሪያ ላደረግንላቸው ጥያቄዎች ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

በዚህም መሰረት ተሰናባቿ አምባሳደሯ መስመር ያላስያዝኳቸው የቤተሰብ ጉዳዮች ስላሉ አስተካከዬ እንድመለስ ፍቃድ ይሰጠኝ ብለው በጠየቁት መሰረት መንግስት ጥያቄያቸውን አጸድቆላቸዋል።

በእጃቸው የነበሩትን የመንግስት ንረቶችንም በሙሉ ለኢምባሲው በተገቢው መንገድ አስረክበው ከሚያዚያ 30 ጀምሮ በእረፍት ላይ መሆናቸውንም አያይዘው ገልጸዋል ።

 

ክብርት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም እስክ መስከረም 30 ድረስ ያለደሞዘ እና ያለ ኢምባሴው ውክለና  በእረፍት ላይ ይቆያሉ ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ተተኪው ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ የጉዞ እና የይለፍ ገደቡ ሲነሳ  በቅርቡ ወደ አውስትራሊያ እንደሚመጡ ይጠበቃል ሲሉ አቶ አቶ በሪሁን ደጉ አያይዘው ገልጸዋል ።


Share

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now