Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

ፈቃዱ ዲኖ፤ መፅሐፍ ሻጩና የኑሮ ትንቅንቅ በአዲስ አበባ

Community
Fekadu Dino. Source: SBS Amharic

ፈቃዱ ዲኖ፤ በቅርቡ ከሱቅ በደረቴ መፅሐፍት አዟሪነት ወደ ባለ አንዲት መደርደሪያ መፅሐፍት ሻጭነት የዞረ ታታሪ ነው። ባለ ትዳርና የዘጠኝ ዓመት ወንድ ልጅ አባት ነው። ባለቤቱ በመንግሥት ድጎማ በወር 1400 ብር ታገኛለች። ፈቃዱ በለስ የቀናው ዕለት 200 ብር አትርፎ ይውላል። አንዲትም መፅሐፍ ሳይሸጥ የሚውልባቸው ቀናትም አሉ። ከቤተሰቡ ጋር የአዲስ አበባን ኑሮ ውድነት የሚገፋው እንዲያ ነው። ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ ስለሆነ "ቁጠባ"ን ከቃልነቱ ባሻገር ንዋይ ሆኖ የባንክ ደብተሩ ላይ ሠፍሮ አይቶ አያውቅም። እንዲያም ሆኖ እንደምን ቤተሰቡንና ደካማ እናቱን እያገዘ "እንደሚኖር" ያወጋል።

Published

By Demeke Kebede

Source: SBS

Share this with family and friends

ፈቃዱ ዲኖ፤ በቅርቡ ከሱቅ በደረቴ መፅሐፍት አዟሪነት ወደ ባለ አንዲት መደርደሪያ መፅሐፍት ሻጭነት የዞረ ታታሪ ነው። ባለ ትዳርና የዘጠኝ ዓመት ወንድ ልጅ አባት ነው። ባለቤቱ በመንግሥት ድጎማ በወር 1400 ብር ታገኛለች። ፈቃዱ በለስ የቀናው ዕለት 200 ብር አትርፎ ይውላል። አንዲትም መፅሐፍ ሳይሸጥ የሚውልባቸው ቀናትም አሉ። ከቤተሰቡ ጋር የአዲስ አበባን ኑሮ ውድነት የሚገፋው እንዲያ ነው። ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ ስለሆነ "ቁጠባ"ን ከቃልነቱ ባሻገር ንዋይ ሆኖ የባንክ ደብተሩ ላይ ሠፍሮ አይቶ አያውቅም። እንዲያም ሆኖ እንደምን ቤተሰቡንና ደካማ እናቱን እያገዘ "እንደሚኖር" ያወጋል።

Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now