መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት ጾም በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እመነት ተካታዮች እየጾሙት ያለውን የአብይ ጾም ሀይማኖታዊ ጠቀሜታውን አስመልከተው ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
አንኳሮች
- አብይ ጾም ፤ ሁዳዴ ፤ ጾመ ኢየሱስ
- ጾም ለሁሉም አማኒ ግዴታ ነውን ?
- በጾም ወቅት ከአማኒያኑ ምን ይጠበቃል ?
መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት ወደ ሀይማኖታዊው አለም ለመጓዝ ፈር የቀደዱላቸው የድጓ መምህር የነበሩት አባታቸው መላከ ሰላም ጥኡመ ልሳን ይልማ እንደሆኑ ይናገራሉ ።
በዝዋይ ገዳም ክህነትን ፤ ቅዳሴን እና ሳታትን ከተማሩ በኋላም ወደ ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በመሄድ የዲግሪ ፕሮግራምን መከታተላቸውን ነግረውናል። ወደ አውስትራሊያ ከመምጣታቸውም በፊትም በአዲስ አበባ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሀላፊ በመሆን ለ17 አመታት አገልግለዋል ።
መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት ላለፉት አምስት አመታት እና አሁንም በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
Share




