በባለቤታቸው አነሳሽነት ከማዕድን ምሕንድስና ወደ ቡና ንግድ ዓለም ዘልቀው የAussie Coffee Roasters ባለቤትና ዳይሬክተር የሆኑት ሚካኤል ፈለቀ የንግድ ድርጅታቸውን ቅዳሜ ኦክቶበር 30 ከ9፡00am እስከ 12፡00pm ለማስመረቅ በመሰናዶ ላይ ናቸው።
የቡና ንግድ ድርጅታቸው መሠረቱ የተጣለው በ2018 ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅት የፐርዝ ከተማ የቡና ንግድ ግልጋሎትን 20 ፐርሰንት የገበያ ባለ ድርሻ ለመሆን በቅቷል።
ኢንጂነር ሚካኤልና ባለቤታቸው በንግዱ ላይ ብቻ ሳይሆን ያተኮሩት፤ የትውልድ አገራቸው ኢትዮጵያ ቡናን ለዓለም ያበረከተች የመሆኗን ታሪክም ለአውስትራሊያውያን ማስተዋወቁን አንዱ ሚናቸው አድርገው ይዘዋል።

Source: M.Feleke

Michael Feleke and his wife. Source: M.Feleke