ለስምንት ቀናት 'ኮማ' ውስጥ ነበርኩኝ፤ እግዚአብሔር ካልረዳ በስተቀር ሰው ከዚህ ውስጥ መውጣት አይችልም" መጋቢ ዘላለም ደስታ

Pastor Zelalem Desta. Source: Z.Desta
መጋቢ (ፓስተር) ዘላለም ደስታ በሜልበርን - አውስትራሊያ የፅዮን ቤተክርስቲያን መሪ፣ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ናቸው። እሳቸውና ቤተሰባቸው እንደምን በኮቪድ- 19 እንደተጠቁ፣ ራሳቸውን ስተው በመተንፈሻ መሳሪያ ከአንድ ሳምንት በላይ እንደምን እንደቆዩ፣ ከሕመማቸው ፅናት የተነሳ ሐኪሞቻቸው በሕይወት ሊቆዩ አይችሉም በሚል ዕሳቤ ላይ እየመከሩ ሳለ እንደምን ወደ ሕይወት ተመልሰው ለቤታቸው እንደበቁ ይናገራሉ።
Share