Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

ግርማ ይፍራሸዋ፤ ከክራር እስከ ፒያኖ ረቂቅ ሙዚቃ

Pianist Girma Yifrashew I.jpg
Pianist Girma Yifrashewa. Credit: G.Yifrashewa

ግርማ ይፍራሸዋ ኢትዮጵያ ስመጥር የፒያኖ ተጫዋችና ሙዚቃ ቀማሪዎች አንዱ ነው። ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት እስከ ሶፊያ ስቴት የሙዚቃ አካዳሚ ዘልቆ በአገርኛና የምዕራባዊያን ረቂቅ ሙዚቃ ተጠብቧል።


Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS



Share this with family and friends


ግርማ ይፍራሸዋ ኢትዮጵያ ስመጥር የፒያኖ ተጫዋችና ሙዚቃ ቀማሪዎች አንዱ ነው። ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት እስከ ሶፊያ ስቴት የሙዚቃ አካዳሚ ዘልቆ በአገርኛና የምዕራባዊያን ረቂቅ ሙዚቃ ተጠብቧል።


አንኳሮች

  • ውልደትና ዕድገት
  • ከሙዚቃ ጋር ፍቅር ላይ መውደቅ
  • ከክራር እስከ ፒያኖ

ግርማ ይፍራሸዋ ከክራር እስከ ፒያኖ፤ ከያሬድ እስከ ባኽ፣ ሞዛርትና ቢትሆቨን ግዘፍ ነስተው በአፍሪካ፣ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ መድረኮች ላይ ናኝተዋል።

በመጪው ወርኅ ኖቬምበር በሜልበርን - አገረ አውስትራሊያ "The Spirit of the Nile" በሚል መጠሪያ ሶስት መድረኮች ተሰናድተውለታል።

Girma Yifrashewa II.jpg
Pianist Girma Yifrashewa. Credit: G.Yifrashewa

እንደ አውስትራሊያውያኑ ሁሉ ኢትዮጵያውያኑም ታድመው ምሽችን በጋራ በጥበብ ሥራው በሐሴት ሊመሉ ይጠብቁታል።

ግርማም መሰናዶውን ከውኖ ታዳሚዎቹን በምዕራባውያኑና አገርኛ ረቂቅ የፒያኖ ጥበብ ሥራዎቹ ከመድረክ እነሆኝ ለማለት ዝግጁ ሆኗል።


Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now