"በኮሮናቫይረስ መያዝ አያሳፍርም፣ የሰውን ክብርም አይቀንስም፤ በግልፅ መናገር አለብን" - ሳባን ዓሊ

Saban Ali. Source: S.Ali
አቶ ሳባን ዓሊ - የሳባን ናያ የሂሳብ ባለሙያ፣ አማካሪና ባለቤት ናቸው። ነዋሪነታቸው በሜልበርን - አውስትራሊያ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኮቪድ 19 ተጠቅተው ወሸባ ገብተው ይገኛሉ። የ10 ቀናት የወሸባ ጊዜያቸው ዛሬ ያበቃል። እንደምን በቫይረሱ እንደተጠቁና እያገገሙ እንደሚገኙ ይናገራሉ። ለኢትዮጵያውያን ማኅበርሰብ አባላትም በኮሮናቫይረስ መያዝ የሚደበቅ ገመና ባለመሆኑ፤ በግልፅ የራስ ተሞክሮን ለሌሎች በመግለፅ የማኅበረሰባዊ ትድግና ሚናቸውን እንዲያበረክቱና ክትባት ለመከተብም እንዳያመነቱ ምክረ ሃሳባቸውን ይለግሳሉ።
Share