ጃኑዋሪ 26 የአውስትራሊያ ቀን?

A Koomurri dancer looks on during the WugulOra Morning Ceremony on Australia Day at Walumil Lawns, Barangaroo on January 26, 2020 in Sydney, Australia. Source: Getty
የዛሬ 234 ዓመት የእንግሊዝ ጦር መርከብ የአውስትራሊያን ምድር ጃኑዋሪ 26 የረገጠባት ዕለት በእንግሊዝ "ሠፋሪዎች" ዘንድ የአውስትራሊያ "ዕለተ ልደት" ሆኖ ሲቆጠር፤ ለነባር የአገሪቱ ባለቤቶች "በወረራ" እና "በሐዘን" ቀንነት ይታሰባል። በየዓመቱም ጃኑዋሪ 26 በመጣ ቁጥር የአውስትራሊያ ቀን በአዎንታዊና አሉታዊ ገፅታው ይነሳል። በአማራጭነትም አውስትራሊያ በፌዴሬሽን አንድ የሆነችበት ጃኑዋሪ 1 ቀን የአውስትራሊያ ቀን ሆኖ ቢክበር ለአገር አንድነት ይበጃል የሚሉ አተያዮችም ጎልተው ይደመጣሉ።
Share