ለታላቅ መሪ የሚያስፈልጉ አምስት ነገሮች
- ርዕይ (Vision) - ትልቅ ሕልም፣ ትልቅ ዓላማ ያለው መሆን። የሚደርስበትን ቦታ የሚያውቅ።
- ለዓላማው ያለው ፍቅር (Passion) - ሕይወቱን ሳይቀር ሊሰዋለት የሚፈልግለት ዓላማ ያለው መሆን።
- ከፍተኛ የማደራጀት ችሎታ (ከሰዎች ጋር የመሥራት ችሎታ)
- ውሳኔ የመስጠት ችሎታ (ለእራስም ቅር የሚያሰኝ ውሳኔን ለድርጅት፣ ለዓላማ ሲባል መወሰን። ኅሊና እየተጨነቀ የሚወሰን ውሳኔን ወዳጅ ላይ፣ በእራስም ደህንነት ላይ የሚወሰኑ ውሳኔዎችን የመወሰን ቆራጥነት)
- ማሳመን (የማዳመጥ፣ የማስረዳት፣ በማሳመን የሰዎችን አመለካከት ተፅዕኖ አሳድሮ የመቀየር ችሎት)
የመሪነት አምስት ደረጃዎች
- ጥሩ ሰው መሆን (ጥሩ ዓላማ፣ ቅንና ችሎታ ያለው ሰው መሆን። ለሀገር፣ ለትውልድ፣ ለእራስ በጎ አሳቢ መሆን፤ ለዚህም ዋጋ መክፈል።)
- በቡድን መሥራት መቻል (ከሰው ጋር መሥራት የማይችል ሰው መሪ መሆን አይችልም። ከትግል አጋሮቹ ጋር ተባብሮ መሥራት መቻል።)
- ማስተባበር መቻል
- ተግባራዊነት
- ውጤታማነትመድረሻውን ማሳየት የሚችል መሪ ነው ጉልበት ያለው። መሪ ተስፋውን ማጋራት፣ ተከታዮቹም እንዲታያቸው ማድረግ አለበት። መሪ ከርዕዩ ሌላ የሚሰጠው ነገር የለውም።ዶ/ር ታደሰ ብሩ
ብዙ ሰው መሪ መሆን ይፈልጋል። ጥቂት ሰዎች ናቸው ተከታይ ለመሆን የተዘጋጁት፤ ነገር ግን መሆን የነበረበት ብዙ ሰው ጥሩ ተከታይ ለመሆን ፈቃደኛ መሆን ነበረበት። ተከታይ ሳይኮን መሪ መሆን አይቻልም።ዶ/ር ታደሰ ብሩ
የጥሩ ተከታይ መመዘኛዎች
- ድርጅታቸው የቆመለትን ዓላማ የሚያስቀድሙ
- ለዓላማው ዋጋ ለመስጠት የቆረጡና ቀድመው ማየት የሚችሉ
- አስተዋፅዖ ለማድረግ የተዘጋጁ
- መሪውን ለማስደሰት ሳይሆን ለዓላማቸው የሚሠሩ
- ኃላፊነት ቢሰጣቸው ሊወስዱ የሚችሉ





