ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ - የኩዊንስላንድ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፀሐፊ፤ የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት።
ዕንቁጣጣሽ ለኢትዮጵያውያን የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን፤ የብርሃን፣ የዕርቅና የፅናት ምልክት ነው።ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ
ያለፈውን ዓመት ውጣ ውረድ ችግርና ፈተናዎች በፅናት አልፈን፣ ለአዲስ ተስፋ ወደፊት የምንገሰግስበት ታላቅ ቀን ነው። አዲስ ዓመት ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለሕዝቧ የሰላም፣ የፍቅር፣ የሕብረትና የብልፅግና እንዲሆን ከልቤ እመኛለሁ።ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ
በአውስትራሊያ እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጵያ የምንገፋፋበት ሳይሆን፤ የምንቀራረብበት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ
።
Share






