SKIP TO MAIN CONTENT

"የመልካም አዲስ ዓመት ምኞቴን በኤምባሲው ዲፕሎማቶችና በራሴ ስም አቀርባለሁ" አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ

Yal G.jpg
Yalelet Getachew, Chargé d'affaires of the Federal Democratic Republic of Ethiopia to Australia. Credit: Y.Getachew

አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ፤ በአውስትራሊያ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ አውስትራሊያውያን የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞትና የመጪ ሥራ ዘመን አገልግሎቶችን ያስመለከተ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።


Published

Updated

By Kassahun Negewo

Source: SBS


Skip to podcast episode content

አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ፤ በአውስትራሊያ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ አውስትራሊያውያን የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞትና የመጪ ሥራ ዘመን አገልግሎቶችን ያስመለከተ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።


በመላው አውስትራሊያ፣ ኒውዝላንድ እና የቀጣናው ሀገራት ነዋሪ የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች፣

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ!

ዕንቁጣጣሽ፣

ዕንቁጣጣሽ የአዲስ ጅማሬ ማብሰሪያ ነው።

በዕንቁጣጣሽ ጨለማው የክረምት ወር ተሸኝቶ መስከረም መጥባቱ ይታወጃል፣ ምድሩ አረንጓዴ ይለብሳል፣ ተራሮች በአደይ አበባ ያጌጣሉ፣ ዜጎችም በአዲስ ተስፋ አዲስ ዕቅድ ያቅዳሉ።

ሀገርም እንደዚሁ ናት።

ኢትዮጵያ ለያዘቻቸው ውጥኖች በአዲስ ተስፋና ጉልበት ለሥራ ትነሳለች።

ያለፈው 2018 ዓም ታላቁ የሕዳሴው ግድባችን ተጠናቆ እና በይፋ ተመርቆ ሙሉ በሙሉ ሥራ የጀመረበት፣ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተካሄደበት፣ ሀገራችን ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች ያካተተ ምክክር ያከናወነችበት ዓመት ነው፡፡

በዚህ የተነሳ አዲሱ ዓመት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ አብላጫ ድምጽ ያገኘው ፓርቲ መንግስት የሚመሠርትበት፣ የሚመሠረተው መንግስት በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚያከናውናቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግባራት የሚያሳውቅበት፣ በሀገራዊ ምክክሩ ስምምነት የተደረሰባቸውን ነጥቦች ለመተግበር ሠፊ እንቅስቃሴ የሚጀመርበት በመሆኑ ለሀገራችን ልዩ ነው።

አባቶቻችን በየዘመናቱ የመጡባቸውን ፈተናዎች በጋራ በመመከት ባሕላቸውን፣ ወጋቸውንና ሥርዓታቸውን ለምዕተ-ዓመታት ጠብቀው በማቆየት አስረክበውናል።

እኛም ልጆቻቸው ከአባቶቻችን የወረስናቸውን የምክክር፣ የመከባበር እና የመቻቻል ጠቃሚ ባሕሎች በማዳበር እንዲሁም ዘመኑን የማይዋጁትን በማሻሻል ለልጆቻችን ጠንካራ አገር የማስረከብ ግዴታችን ልንወጣ ይገባል።

ለእዚህም በውጭ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድርሻቸው የጎላ እንደሚሆን እናምናለን።

በመሆኑም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዲሱን ዓመት ስናከብር ነገ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት እያንዳንዳችን ማበርከት የሚጠበቅብንን አስተዋጽዖ ቆም ብለን በማሰብ እንዲሆን ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

ዜጎቻችንና የኢትዮጵያ ተወላጆች በአውስትራሊያና በአካባቢው ሀገራት የተለያዩ ተቋማት የምታስመዘግቧቸው አመርቂ ውጤቶች ከሀገራቱ ጋር ያለንን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከቀን ወደ ቀን እያላቀው በመሆኑ ኤምባሲው እንደሚኮራባችሁ ለመግለጽ እንወዳለን።
አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ

በመጨረሻም ካንቤራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመጭው ዓመት የተሳለጠ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የዲጂታላይዜሽን ሂደቱን እያጠናቀቀ ሲሆን፣ አገልግሎታችን በያላችሁበት፣ ባጠረ ጊዜ እና ወጭ ቆጣቢ በሆነ አግባብ ተደራሽ ይሆን ዘንድ ከሁሉም አደረጃጀቶች ጋር በጋራ ለመሥራት ኤምባሲያችን እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ ዛሬም ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል።

በመሆኑም በኢንቨስትመንት፣ በንግድና ቱሪዝም መስኮች ላይ በንቃት በመሳተፍ የሀገራችንን ዕድገት በጋራ ዕውን እንድናደርግ ግብዣዬን እያቀረብኩ የመልካም አዲስ ዓመት ምኞቴን በኤምባሲው ዲፕሎማቶችና በራሴ ስም በድጋሚ አቀርባለሁ።

አመሰግናለሁ።


Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now