ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት ፕሬዚደንት፤ በሀገር ውስጥና በባሕር ማዶ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት።
ከሁሉም በላይ በእዚህ በአዲሱ ዓመት ለሀገራችንና ለሕዝባችን ሰላም እንዲወርድልን እግዚአብሔርን መለመን ተገቢ ነው። ጦርነት፣ መከፋፈልና ችግር እጅ ለእጅ ተያይዘው በኢትዮጵያ ምድር ለበርካታ ዘመናት ዕንባ አስፈስሰውናል፤ በስደት እንድንበታተን አድርገውናል። ይህ እንዲቆም ሰላሙን፣ ፍቅሩን፣ አንድነቱንና በረከቱን ፈጣሪ ይመልስልን።ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት ፕሬዚደንት
Share






