ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው - በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ አዲሱን 2019 የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ ሕዝባዊ በዓል ምክንያት በማድረግ መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።
መጪው ዓመት ሁሉንም አካላት አሸናፊ የሚያደርግ፣ ሁሉም ሕፃናት ወደ ትምህርት ገበታቸው የሚመለሱበት፣ የሀገራችን አንድነት የሚፀናበት፣ የሰዎች ማንነት የኩራታቸው ምንጭ ብቻ የሚሆንበት፣ የወጣቶች ስደትና መከራ የሚቆምበት፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የማይታይበት፣ መሪዎቻችን ሕዝባቸውን በቅንነት የሚያገለግሉበት፣ ወጣቶቻችን መጪው ዘመን የእነሱ እንደሆነ አውቀው ኃላፊነት የሚወስዱበት ዘመን እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን ለመግለፅ እወዳለሁ።ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው - በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት
Share






