Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

" እኛ ወንጀለኞች አይደለንም በዘመናዊ እስር ቤት እንዳለን ነው የተሰማን" በፍላሚንግተን እና ኖርዝ ሜልበርን በሚገኙት የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች

.

LR-Yonatan ,Ephrem and Betelehem. Source: Supplied

በቪክቶሪያ የኮቪድ19 ( COVID-19 ) ስርጭት ለመግታት የፕሪምየር ዳንኤል አንድሪው መንግስት በሜልበርን የሚገኙ ዘጠኝ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ዝግ እንዲሆኑ እና በውስጣቸው የሚኖሩ 3000 ያህል ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ አግዷል፡፡ ይህንንም ለማስከበር 500 ፓሊሶችን በስፍራው አሰማርቷል ፡፡


Published

Updated

Source: SBS


Share this with family and friends


በቪክቶሪያ የኮቪድ19 ( COVID-19 ) ስርጭት ለመግታት የፕሪምየር ዳንኤል አንድሪው መንግስት በሜልበርን የሚገኙ ዘጠኝ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ዝግ እንዲሆኑ እና በውስጣቸው የሚኖሩ 3000 ያህል ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ አግዷል፡፡ ይህንንም ለማስከበር 500 ፓሊሶችን በስፍራው አሰማርቷል ፡፡


በፍላሚንግተን እና ኖርዝ ሜልበርን በሚገኙት የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ሙሉ ለሙለ ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ  ትእዛዝ ወጥቷል ፡፡የቪክቶሪያ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለጊዜው ያለው ብቸኛው መፍትሄ ነው ብሎ ቢያቀርብም ነዋሪዎች ግን  ሁኔታውን በተለያየ መንገድ ነው የሚያዩት ፡፡ በተለይ እንደሌሎች አካባቢዎች በቂ የመዘጋጃ ጊዜ ሳይሰጠን እገዳው በፍጥነት መደረጉ እና እንዳንንቀሳቀስ  በፖሊስ ጥበቃ ውስጥ መውደቃችን አግባብ አይደለም ፡፡እኛ ወንጀለኞች አይደለንም እንደውም በዘመናው እስር ቤት እንዳለን ነው የተሰማን  ሲሉ ቅሬታቸውን ያጋሩን ዮናታን ይስሃቅ እና ቤተልሄም በዛብህ ከፍላሚንግተን እንዲሁም አቶ ኤፍሬም ሹምዬ ከኖርዝ ሜልበርን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ናቸው፡፡


Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now