የእግር ኳስ ኮከቦቹ ኤርሊንግ ሃላንድ እና ኪሊያን ምባፔ ፦ እያንዳንዳቸው ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ኖርዌይንና፤ ፈረንሳይን ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፉ አድርገዋል።
አንኳሮች
- የ20ኛው ቀን የፊፋ የዓለም ዋንጫ በዳላስ በተካሄደ አስደናቂ የ32 ዙር ጨዋታ ፤ ኖርዌይ ኮትዲቯርን 2 ለ1 አሸንፋ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች።
- በኒው ጀርሲ ፈረንሳይ -ስዊድንን 3 ለ0 በማሸነፍ ወደ 16 ዙር አልፋለች ፤ሁለቱንም ግቦች ያስቆጠረውም ካፒቴኑ ኪሊያን ምባፔ ነው
- የአውስትራሊያ ብሔራዊ ቡድን (ሶከሩስ) በ32ተኛው ዙር ከግብፅ ጋር ለሚያደርገውን ጨዋታ ዳላስ ደርሷል
- በሐሙስ፣ በ21ኛው የዓለም ዋንጫ ቀን፣ እንግሊዝ ከዲ.አር. ኮንጎ ጋር ትጫወታለች፤ ቤልጂየም ደግሞ በምድብ ጨዋታዎች ከሶስተኛ ደረጃ ቡድኖች መካከል በተሻለ ውጤት በማለፍ ከሴኔጋል ጋር ትገናኛለች
Share





