የፊደል ገበታ
አቶ ዳባሳ ፊደል መቁጠር የጀመሩት ዘግይተው ነው። ሆኖም ከክፍል ክፍል ቀልጥፈው በመሸጋገር የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የፈፀሙት የኢሕዲሪ (ደርግ) ሥርዓት በኢሕአዴግ ተተክቶ ሳለ ነው።
Advertisement
በዚያም አላበቁም ከጅማ እርሻ ኮሌጅ በእርሻ ትምህርት በዲፕሎማ ተመርቀዋል።
Dabessa and his freinds in Jimma Agricultural College - 1993 (F-L). Source: D.Waqjira
የሥራ ዓለም
በወቅቱ በቁቤ አፋን ኦሮሞ ሰልጥነው ነበርና ክህሎታቸው ለአስተማሪነት፣ ሲልም ለማዘጋጃ ቤት ተቀጣሪነት አብቅቷቸዋል።
የማዘጋጃ ቤት ሠራተኛ ሆነው ሳለ እ.አ.አ በ1994 የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሥራ ማስታወቂያ አወጣ።
አመለከቱ። ተወዳድረውም አለፉ።
የኮሌጅ ትምህርታቸው ዋቤ ሆኗቸው በኦሮምኛ ዝግጅት ክፍል ለእርሻ ጋዜጠኛነት በቁ።
በእርሻ ሪፖርተርነት ሳይወሰኑ የሁሉም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቋንቋ ማዕከል አስተባባሪ እርክን ላይ ደረሱ።
ሥራቸው ላይ እያሉ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘልቀው የጋዜጠኛነት ሙያ ዕውቀት ቀሰሙ።
Graduation ceremony at Addis Ababa University - 1998. Source: D.Waqjira