ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

ዳባሳ ዋቅጅራ፤ ከስደት ወደ ሠፈራ

ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Community

Dabassa Waqjira and his family.


Published 24 June 2022 at 10:44pm
By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

አቶ ዳባሳ ዋቅጅራ ከሶስት ልጆቻቸው ጋር አውስትራሊያ ዘልቀው ሳይረጋጉ ባለቤታቸው ላይ የ10 ዓመት እሥር ብይን መጣሉን ሰሙ። በጠበቆቻቸው አማካይነት ይግባኝ አሉ። በለስ ቀናቸው። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ክሱን ውድቅ አደረገ። ባለቤታቸው ከሶስት ዓመታት እሥራት በኋላ በነፃ ተለቀቁ። ሁለት ዓመታት ቆይተው አውስትራሊያ እንዲሠፍሩ ይሁንታን አገኙ። ባልና ሚስት ከተለያዩ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ዳግም በአንድ ጣራ ስር መኖር ጀመሩ።


Published 24 June 2022 at 10:44pm
By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS


ባልና ሚስቱ አንድ አልጋ መጋራት በጀመሩ በዓመቱ አንድ ልጅ አፈሩ። 

በአሁኑ ወቅት የመጀመሪያ ትልቋ ልጃቸው ከዩኒቨርሲቲ ተመርቃ ሥራ ላይ ተሠማርታ ትገኛለች።

ሁለተኛ ልጃቸውና ሶስተኛ ልጆቻቸው የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ላይ ይገኛሉ። 

Advertisement
 የአውስትራሊያ ፍሬ የሆነችው የመጨረሻ ልጃቸው የሁለተኛ ክፍል ተማሪ ናት።


Share