የኢትዮጵያ 2013 አገር አቀፍ ምርጫና የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ፋይዳ ምንድን ናቸው?
- ኢትዮጵያ ችግር ውስጥም ብትኖር፤ የምርጫው ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ መሆን ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ ነው። ለአሸነፈው ፓርቲም ዕውቅናን ይሰጣል።
- ጋዜጠኛ መሐመድ አባዋጂ

Journalist Mohamed Abawaji. Source: M.Abawaji
- የኢኮኖሚና የበጀት ምንጭ የሆኑት አገራት በዚህ ማዕቀፍ አለማለፍ አስቸጋሪ ሁኔታ ይፈጥራል። ሕዝብን እያጠፋ ምርጫን ለስልጣን ማቆያ ካርድ መጠቀም አታላይነት፤ አስመሳይነት ነው።
- ኃይሌ አረፈዓይኔ

Haile Arefeayne. Source: H.Arefeayne
- በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ታጣቂዎች ነፃ መሬት ይዘው ሕዝብን እያፈናቀሉ፣ እየገደሉ፣ ሰብዓዊ ቀውስ እያደረሱ ባለበት፤ ፖለቲካዊ ምሕዳሩ በአንፃራዊነት በጠበበት፣ ኮሮናቫይረስ በእጅጉ በተስፋፋበት፣ የምርጫ ቦርድ የዝግጅት ውስንነት ባለበት ሁኔታ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታ አለ ብዬ አላስብም። መካሄድ አለበትም ብዬ አላምንም።
- ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ መኮንን

Dr Laychiluh Bantie Mekonnen. Source: LB.Mekonnen
- አንድ ፓርቲ 96፣ 99 እና 100 ፐርሰንት አሸነፍኩ ሲል በታዛቢነት የመጡ አፅድቀው ነው የተመለሱትና ያን ያህል አሳሳቢ አይመስለኝም።
- በእኔ ዕይታ አገሪቱ ከገባችበት ችግር አንፃር ምርጫ የቅንጦት ነው። በዚህ ምርጫ ምክንያት ዘውግ ተኮር ጥቃት ሊያገረሽ ይችላል። ምርጫው በሰላም ከተጠናቀቀ አገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የኅብረብሔራዊ ፓርቲ ፓርላማዊ ግንኙነት ሊኖራት ይችላል። ሕገ መንግሥቱን ለማሻሻል ቅቡልነት ያስገኛል።
- ዶ/ር ተበጀ ሞላ

Dr Tebeje Molla. Source: T. Molla