አማራጭ መፍትሔዎች
- የኢትዮጵያ መንግሥትም ሕወሓትም ጦርነት ያቆሙ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሁሉም ባለድርሻዎች ጋር ተቀምጠው ይነጋገሩ
- ልዩነቶቻችንን በማጥበብ በጋራ በሚያስማሙን ጉዳዮች ላይ እናተኩር
- ዶ/ር ዑስማኢል ጎርሴ

Dr Ismail Gorse. Source: I.Gorse
- ንግግር ሲባል የአንድ ወገን ብቻ ሆኖ መታየት የለበትም
- ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ አማራጮች መፍትሔ አይሆኑም
- ሉዓላዊነትን ለማስከበር ሲባል ማድረግ የማንሻው ቢሆን እንኳ ማድረግ ግድ የምንሰኘበትም ሁኔታ ሊኖር ይችላል
- ወ/ሮ ማሜ ወርቁ

Mamay Worku. Source: M.Worku
- ጦርነት አማራጭ አይሆንም፤ ለሰላም የሚከፈል መስዋዕትነት ያስፈልጋል
- ሕገ መንግሥቱን የምንጠራ ከሆነ ሕገ መንግሥቱን እየጠራን፤ ታሪክም የምንጠራ ከሆነ ታሪክ እየጠራን ያሉንን ችግሮች እየጠራን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት መቻል አለብን
- እያንዳንዱ ክልል ሕዝበ ውሳኔ ማካሔድ አለበት
- ደጀን የማነ

Dejen Yemane. Source: D.Yemane