ወ/ሮ ማሜ ወርቁ - በዩናይትድ ስቴትስ ዌስት ኮስት የሕዝባዊ ዲፕሎማሲ ሰብሳቢ፣ ዶ/ር ዑስማኢል ጎርሴ - የኢትዮጵያ ሶማሌ ዲሞክራሲያዊ ፎረም ሊቀመንበርና ደጀን የማነ - በኒው ሳውዝ ዌይልስ ዩኒቨርሲቲ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ፤ በኢትዮጵያ መንግሥት የተናጠል ተኩስ ማቆም ዕወጃና ለትግራይ ቀውስ ሰላማዊ መፍትሔ ፍለጋ ሂደት ላይ አተያያቸውን ያንጸባርቃሉ።
ተኩስ አቁም
“የኢትዮጵያ መንግሥት የተናጠል ተኩስ ማቆም ለሕዝብ ያለውን ጥንቃቄ፣ ዕይታና ዘላቂ ተፅዕኖዎች አርቆ የማየት ችሎታን የሚያመላክት ይመስለኛል። ውሳኔው ለትግራይ ሕዝብ፣ ለሚዲያ ለማኅበራዊ ሚዲያና ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም መልዕክት መላክ ይመስለኛል።” ወ/ሮ ማሜ ወርቁ

“የኢትዮጵያ መንግሥት ምንም እንኳ የተናጠል ተኩስ ማቆም እርምጃ ቢወስድም ጦርነቱ ገና አልቆመም። መንግሥት ጦሩን እያሰባሰበ ነው።” ዶ/ር ዑስማኢል ጎርሴ

“መንግሥት የወሰደው ውሳኔ የጦርነቱን አቅጣጫ ቀየረ እንጂ ተኩስ አላቆመም።” ደጀን የማነ







