"ኢትዮጵያ ውስጥ በአገራዊ ድርድር ለመሳተፍ ትጥቅ ታጥቀው ያሉ አካላት እንደ ቅድመ ሁኔታ ትጥቅ መፍታት አለባቸው" ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ

Community

Rifles. Source: Getty

"ድርድሩ የተሳካ እንዲሆን ሁሉንም ያካተተ መሆን አለበት። ትጥቅ ፍታና አትፍታ የሚለው ጉዳይ መቅረብ የለበትም። ምክንያቱም አንዱ በፌዴራል መንግሥቱ ከለላ የሚደረግለት ማኅበረሰብ ሲሆን፤ ሌላኛው በፌዴራል መንግሥቱና በሌሎች የሚጨፈጨፍ ማኅበረሰብ ባለበት ትጥቅ ፍታ ማለት ኢፍትሐዊና ኢሰብዓዊ ይመስለኛል" ደጀን የማነ


ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ፤ በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የመድኃኒት ጥናትና ግኝት ተመራማሪና ደጀን የማነ በኒው ሳውዝ ዌይልስ ዩኒቨርሲቲ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ የውይይት መድረካችን ተሳታፊዎች ናቸው። የውይይት አጀንዳዎቻችን የአገራዊ ምክክር አሥፈላጊነትና ፋይዳዎች፣ በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተደረሰው ጊዜያዊ ከግጭት የመታቀብ ስምምነትና በሩስያና ዩክሬይን የመረረ ጦርነት ውስጥ ሆኖ የተኩስ ማቆም ድርድር ጥረቶች ተምሳሌነቶች ናቸው። ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።


  

አንኳሮች


 

  • ተደራዳሪ ባለ ድርሻ አካላት
  • ባለ ትጥቅና ትጥቅ አልባ ተደራዳሪዎች
  • አማራጭ መንገድ

Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service