ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ፤ በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የመድኃኒት ጥናትና ግኝት ተመራማሪና ደጀን የማነ በኒው ሳውዝ ዌይልስ ዩኒቨርሲቲ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ የውይይት መድረካችን ተሳታፊዎች ናቸው። የውይይት አጀንዳዎቻችን የአገራዊ ምክክር አሥፈላጊነትና ፋይዳዎች፣ በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተደረሰው ጊዜያዊ ከግጭት የመታቀብ ስምምነትና በሩስያና ዩክሬይን የመረረ ጦርነት ውስጥ ሆኖ የተኩስ ማቆም ድርድር ጥረቶች ተምሳሌነቶች ናቸው። ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
"ከሩስያና ዩክሬይን ችግሮች በጦርነት እንደማይፈቱ በመረዳት ድርድር ማካሄድንና ሕዝባዊ የጦርነት ተቃውሞን ልንማርበት እንችላለን" ደጀን የማነ

Ukrainian Defence minister Oleksii Reznikov (L) shakes hands with Russian negotiators prior the talks between delegations from Ukraine and Russia in Belarus. Source: Getty
"በብልፅግናና ሕወሓት በኩል የዩክሬይንና የራሽያ ልዑካን የሚያደርጉትን ዓይነት ፖለቲካዊ ድርድር በጦርነት መሃል ለማድረግ ፍላጎቱም የዕሳቤ ደረጃውም አላቸው ብዬ አላስብም" ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ
Share