ለወቅታዊው የኢትዮጵያ ችግሮች መንስዔዎቹ ምንድናቸው?
- ስልጣን በለቀቀው አካል ሕወሓትና ኢትዮጵያን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር ራሱን ብልፅግና ብሎ በሚጠራው መካከል የተፈጠሩ ችግሮች ናቸው።
- ጋዜጠኛ መሐመድ አባዋጂ

Journalist Mohamed Abawaji. Source: M.Abawaji
- አሃዳዊነት - አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ብሔር ለመመሥረት የሚካሄድበት መንገድ አሁን ወዳለንበት ደረጃ አድርሶናል።
- ኃይሌ አረፈዓይኔ

Haile Arefeayne. Source: H.Arefeayne
- አሁን ለደረሰው የሰብዓዊ ቀውስ፣ ዲፕሎማሲያዊ ቀውስና ፖለቲካዊ ቀውስ ምክንያቶቹ በሕዝብ ትግል የመጣን ለውጥ ለራሳቸውና ለቡድናቸው ያተኮሩ ቡድኖች ከሕዝብ ጠልፈው ለራሳቸው መውስዳቸው ነው።
- ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ መኮንን

Dr Laychiluh Bantie Mekonnen. Source: LB.Mekonnen
- በመሃል አገር መንግሥትና በክልላዊ አስተዳደር መንግሥት የነበረ ቁርሾ፣ የዓባይ ግድብና ዓለም አቀፍ ኃይሎች የፈጠሩት ጫናዎች፣ የዘር ተኮር ጥቃቶችና የኢኮኖሚ ድቅቀት ለቀውስ አድርሶናል።
- ዶ/ር ተበጀ ሞላ

Dr Tebeje Molla. Source: T.Molla