ዶ/ር ተበጀ ሞላ - በዲከን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፖሊሲና የማኅበራዊ ፍትሕ ተመራማሪ፣ ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ መኮንን - በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የመድኃኒት ግኝትና ቅመማ ጥናት ተመራማሪ፣ ኃይሌ አረፈዓይኔ - በሳውዘርን ክሮስ ዩኒቨርሲቲ የከርሰ ምድር ውኃና ማዕድን የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪና ጋዜጠኛ መሐመድ አባዋጂ ኢትዮጵያን ገጥመዋት ላሉ ችግሮች አማራጭ ይሆናሉ የሚሏቸውን ምክረ ሃሳቦች ያጋራሉ።
ለወቅታዊው የኢትዮጵያ ችግሮች አማራጭ መፍትሔዎች ምንድናቸው?
- የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው፤ እያንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብ ቁጭ ብሎ ተወያይቶ፣ ያጠፋም ተጠያቂ እንዲሆን የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎች አንድ ላይ ከመጡ ነው።
- ጋዜጠኛ መሐመድ አባዋጂ

- አንደኛው የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ አውቆ ወደፊት መሄድ ነው
- ሌላኛው ትግራይ ላይ ለደረሰው ጭፍጨፋ ጥፋተኛ የሚባለው ሁሉ የሚቀጣበትን መንገድ ማስተካካልና ብዝኅነታችንን መቀበል መቻል ነው።
- ኃይሌ አረፈዓይኔ

- ኢትዮጵያዊ ችግሮችን ለመፍታት ዋናውና ትልቁ ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ
- ከሁለት እስከ ሶስት ዓመታት የሚቆይ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የሽግግር መንግሥት መመስረት
- ከዚያም ወደ ዲሞክራሲያዊ የምርጫ ሥርዓትና ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሄድ ነው።
- ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ መኮንን

- ከትግራይ ቀውስ ጋር በተያያዘ ባልታጠቁ ሰዎችን ላይ ደረሱ የተባሉ ወንጀሎችን መርምሮ ለሕዝብ የሚያቀርብ ነፃና ገለልተኛ አጣሪ ወደ ማሰማራት
- የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ምድር ለቅቆ እንዲወጣ ማድረግ
- የዘውግ ፖለቲካን ለማስወገድ ጂኦግራፊን፣ ኢኮኖሚንና ባሕላዊ ትስስርን ማዕከል ያደረገ የፌዴራሊዝም አደረጃጀት ማድረግና
- የግጭት መንስኤ የሆኑ መሬቶች ላይ ሕዝበ ውሳኔ ማካሄድ ይገባል።
- ዶ/ር ተበጀ ሞላ

Share






