ዶ/ር ተበጀ ሞላ - በዲከን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፖሊሲና የማኅበራዊ ፍትሕ ተመራማሪ፣ ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ መኮንን - በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የመድኃኒት ግኝትና ቅመማ ጥናት ተመራማሪ፣ ኃይሌ አረፈዓይኔ - በሳውዘርን ክሮስ ዩኒቨርሲቲ የከርሰ ምድር ውኃና ማዕድን የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪና ጋዜጠኛ መሐመድ አባዋጂ ኢትዮጵያ ላይ የተጣሉትን ገደቦች አስባብና አሳሳቢነት አንስተው ይናገራሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ላይ የጣለቻቸው ገደቦች ጫና ምን ያህል አሳሳቢ ናቸው?
- የአሜሪካ [ጫና] የዓለም ገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ የሚሰጡትን ድጎማ ለተወሰነ ጊዜ ማስቆም ነው። ይኽን በማድረግ ኢትዮጵን መቀየር አትችልም።
- ጋዜጠኛ መሐመድ አባዋጂ

- በጀቷ በእርዳታ ላይ የተንጠለጠለን አገር ይዞ ማዕቀቡ ፋይዳ የለውም ማለት በትንሹ አሳንሶ ማየት እንዳይሆን።
- ኃይሌ አረፈዓይኔ

- የኢትዮጵያ መንግሥት የፈጠራቸው የአካሄድ ስህተቶች፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎችን ጨምሮ የተነሳባቸው መነሻዎች አሁን እየደረሰብን ላሉት የዲፕሎማሲ ጫና ትልቅ መሰረት ነው።
- ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ መኮንን

- እንደታሰበው የኢኮኖሚ ማዕቀቦች ከተከተሉ በአገሪቱ ላይ የሚያደርሰው ቀውስ የከፋ ነው የሚሆነው።
- ዶ/ር ተበጀ ሞላ

Share






