ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ፤ በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የመድኃኒት ጥናትና ግኝት ተመራማሪና ደጀን የማነ በኒው ሳውዝ ዌይልስ ዩኒቨርሲቲ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ የውይይት መድረካችን ተሳታፊዎች ናቸው። የውይይት አጀንዳዎቻችን የአገራዊ ምክክር አሥፈላጊነትና ፋይዳዎች፣ በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተደረሰው ጊዜያዊ ከግጭት የመታቀብ ስምምነትና በሩስያና ዩክሬይን የመረረ ጦርነት ውስጥ ሆኖ የተኩስ ማቆም ድርድር ጥረቶች ተምሳሌነቶች ናቸው። ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
"የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው በአገራዊ ምክክር ሳይሆን ሁሉን አካታች በሆነ ድርድር ነው" ደጀን የማነ

Dr Laychiluh Bantie (L), and PhD Candidate Dejen Yemane. Source: Bantie and Yemane
"በውሸት የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት ሰፋፊ መፈናቀሎች፣ ስር የሰደዱ ጥላቻዎችና ግድያዎች ሊፈቱ የሚችሉት በአገራዊ ውይይት፣ መግባባትና ድርድር ነው" ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ
Share