ምልሰታዊ ምልከታ 2019 - ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና ዶ/ር አምባቸው መኮንን

Dr Ambachew Mekonnen (L), and Dr Negasso Gidada (R) Source: Courtesy of PD
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በአገረ ጀርመን በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በወርሃ ኤፕሪል መገባደጃ 2019 ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ዶ/ር አምባቸው መኮንን፤ የአማራ ብሔራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድርም በፖለቲካ ተቃናቃኞቻቸው እጅ ሕይወታቸው በወርኃ ጁን 2019 አልፏል። በ2019 የምልሰት ምልከታችን ቀደም ሲል ከሁለቱ መሪዎች ጋር አድርገናቸው ከነበሩት ቃለ ምልልሶች ቀንጭበን አቅርበናል።
Share