"ከሞትኩ በኋላ ሰው ላይ ክፋት የማይሠራ ሰው ብለው ቢያስቡኝ ይበቃኛል" - ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

Prof Getachew Haile. Source: G.Haile
ጁን 10, 2021 ከዚህ ዓለም ለዘላለሙ ተሰናብተው ጁን 18, 2021 በአገረ አሜሪካ ቅዱስ ዮሐንስ ገዳም የሚያርፉት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፤ በቤተሰባቸው ልብ ውስጥ ማንም ሊሞላው የማይችለው ክፍተት መፍጠራቸው እውነት ነው። በሕይወት ሳሉ በተለይም ባለቤታቸውን ወ/ሮ ምሥራቅን ከሕይወታቸው ነጥለው አያዩ ስለነበር "ባለቤቴ ቆንጆ፣ ጨዋ፣ ለቤተሰብዋ ማንኛውንም ነገር አድርጋ መጨረሻ የምታገለግለው ራሷን ነው። ለኔ ሕይወቴ ነች" ብለው ነበር የሚገልጧቸው። እርግጥ ነው፤ ፕ/ር ጌታቸው በሥራዎቻቸውና የአገር ፍቅር ስሜታቸው ከሕይወት በኋላ ይኖራሉ።
Share