አንኳሮች
- ውልደትና ዕድገት
- ከነቀምቴ እስከ አውስትራሊያ
- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጋይነት
- ማኅበረሰባዊ ድጋፍ ለአቶ ሩፋኤል መንታ ልጆች
ሩፋኤል ሰውን በጣም ያከብራል፤ ተጫዋች ነው። ከሰው ጋር ከተገናኘ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ዘላቂ ትውስታን ፈጥሮ የሚሔድ ነው። ምኞቴ የ10 ዓመት መንታ ልጆቹ አድገው፤ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲያልፉ አይቶ ቢያልፍ ነበር።ነርስ ያደሳ በዳሳ
ሩፋኤል ፈገግታው የማይረሳ፣ ከሁሉም ሰው ጋር የሚግባባ፣ የተቸገረ ሰው ለመርዳት የመጀመሪያ ረድፍ ላይ ሰልፍ የሚቆም፣ የፍቅር ሰው፤ ተወዳጅ ሰው ነበር።የመድረክ መሪና ዲጄ ከሪም ዲጋል
ሩፋኤል በጣም ደግ ሰው፣ ከሁሉ ሰው ጋር ተግባቢ፣ እሱ ያለበት ቦታ ጨዋታና ሳቅ አለ። ለኦሮሞ ሕዝብ በጣም አሳቢና ታጋይ ነበር። በሽታውን እንኳ ለሰው በመናገር ማስቸገር አይፈልግም ነበር።አርቲስትና የአዕምሮ ጤና ባለሙያ ኩመላ አዱኛ
እንደ ኦነግ ሆነ እንደ ራሴ ሐዘናችን ከባድ ነው። ልባችን ተሰብሯል። ሩፋኤል ትግሉ ውስጥ የነበረው ከልጅነቱ ጀምሮ ነው። ሕዝቡን በጣም የሚወድ ሰው ነበር። ለቤተሰቡና ለማኅበረሰቡ እግዚአብሔር መፅናናትን እንዲሰጣቸው እጠይቃለሁ።ኦቦ ዳኜ ደፈርሻ





