"በሚስጥር ከማኅበረሰቡ ውስጥ ተነቅለው የወጡ እውነቶችን የያዘ ነው፤ በሚስጥር ያደረግነው ነገር በአደባባይ ያስለቅሰናል ነው ፅንሰ ሃሳቡ" ሶፎኒያስ ታደሰ

Secret TV Drama.png

Credit: Abol

በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ፀሐፊ፣ አዘጋጅ፣ ዳይሬክተርና መምህር ሶፎኒያስ ታደሰ፤ በቅርቡ በአቦል ቴሌቪዥን ለታዳሚዎች ዓይነ ገብ ለመሆን የዕይታ መሰናዶው ስለተጠናቀቀለት ባለ 260 ክፍል ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ጭብጥ ቀንጭቦ ያጋራል።


አንኳሮች
  • የፊልም ትምህርት ቀሰማ በደቡብ አፍሪካ
  • የፊልም ሥራ ጅማሮ
  • በሚስጥር
ደቡብ አፍሪካ እጅግ የዘመነ የቴሌቪዥን ኢንዱስትሪ አላት። እኛ - ምናልባት ለፍተን ከሠራን የደቡብ አፍሪካ የቴሌቪዥን አብዮት ላይ ለመድረስ፤ ከእዚህ በኋላ ከ60 እስከ 70 ዓመት ይፈጅብናል ብዬ አስባለሁ።
ሶፎኒያስ ታደሰ
ትልቁ ሕልሜ ልክ እንደ ደቡብ አፍሪካ አንድ ፊልም ላይ በተለያዩ ቋንቋዎች መሥራት ነው። ይህንን አሳክቼ በነገታው ባንቀላፋ አይቆጨኝም።
ሶፎንያስ ታደሰ
ትልቁ ቁጭቴ ምንድን ነው?! 'ኢትዮጵያውያኖች ታሪክ ነጋሪ አይደሉም ወይም ረጅም ታሪክ የመገንባት አቅም የላቸውም' ተብሎ ይታመናል። እኔም ብሆን በከፊል አምንበታለሁ። ግን ደግሞ ማሸነፍ እንችላለን ብዬ አምናለሁ። ኢትዮጵያውያኖች ለ10 ዓመት፣ ለ20 ዓመት የሚታይ ድራማ የመፃፍ አቅም አለን የሚለውን ማሳየት እፈልጋለሁ።
ሶፎንያስ ታደሰ

Share

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now