ወርኃ ፅጌና ጋቢ

Flower, Surrounding of Hawasa, Ethiopia. Source: Getty
በወርኃ ፅጌ የጥቅምት አበባዎች በምድረ ኢትዮጵያ ፈክተው ደምቀው ይታያሉ። ብርዱንም ተከትሎ ጋቢ ድረባ አንዱ አገርኛ አለባበስ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የአድዋ ዘመቻ መሰባሰቢያ የሆነችውን የወረኢሉን ከተማን ለማስተዋወቅና ባሕላዊ የጋቢ አለባበስ ዕሴትንም ለማጉላት "በጥቅምት ዕኩሌታ፤ አንድ ኩታ" በሚል አሰባሳቢ ቃል በአገር ውስጥና በባሕር ማዶ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ባሕላዊ የማንቂያ ዘመቻ እየተካሔደ ነው። የእርስዎና ጋቢ ቅርበት ምን ይመስላል? ከጥቅምት 22 እስከ ኅዳር 6, 2014 የሚዘልቅ "መፅሐፍትና ኩታ" በሚል የመፅሐፍ አውደ ርዕይ በብሔራዊ ቲያትር በረንዳ ላይ ይካሔዳል።
Share