ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ከዲሴምበር 24 - 28 / ታህሳስ 15 - 19 በሜልበር ከተማ ስለሚከበረው ዓመታዊው 29ኛ የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ውድድር ሂደትና ተልዕኮ ይናገራሉ። አ ምስት ቀናት የሚፈጀው ዓመታዊው የስፖርት በዓል የሚከናወነው Arndell Parke Reserve, 49 Federation Blvd, Truganina ነው።
አንኳሮች
- የተወዳዳሪ ቡድኖች ቁጥርና ተሳትፎ
- ዓመታዊ የስፖርት ውድድሮችን በየክፍለ ሀገሩ የማዟዟር ዕሳቤ
- መርሃ ግብሮች
- "ባትገዙም ጠይቁን"
- የግለሰቦችና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች ተሳትፎዎች
ማኅበረሰቡን መጠየቅ አለብን፤ ግን አንለምንም። ያን የምናደርገው አገልግሎት በመስጠት ነው።ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
ሌላ ቦታ የማናገኘው የኢትዮጵያን ቡናና የምግብ ሽታ ነው።የሶማሌ ማኅበረሰብ አባላት
Share






