ተኩስ አቁም
“የረጅም ጊዜ አዎንታዊ ተፅዕኖው ወደፊት የሚታይ ሆኖ፤ መንግሥት የወሰደውን የአንድ ወገን ተኩስ አቁም የምመለከተው በአዎንታዊ ጎኑ ነው። የመንግሥትን ሆደ ሰፊነትና ቻይነት የሚያሳይ መልካም ራዕይ ያለው ውሳኔ ነው።” አቶ አዳሙ ተፈራ
“የፌዴራል መንግሥቱ ተኩስ አቁሜያለሁ ብሎ ቢያውጅም፤ የእርዳታ ክልከላው፣ የቴሌኮም ክልከላው፣ ድልድይ መስበሩና ባንክ እንዳይንቀሳቀስ ማድረጉ አልቆመም። ጦርነቱ መልኩን ቀየረ እንጂ የፌዴራል መንግሥቱ ጦርነቱን አስቁሞታል የሚል ዕምነት የለኝም።” ዶ/ር ፍሳሃ ኃይለ ተስፋይ
“የተወሰደው የተኩስ ማቆም ሰከን ብለን ከዚህ ቀውስ ውስጥ እንዴት እንወጣለን ብሎ ለማሰብና ወደ ፖለቲካዊ መፍትሔ ለመሔድ ዕድል ይሰጣል ብዬ አስባለሁ።” አቶ አያሌው ሁንዴሳ
ሰላማዊ መፍትሔ

Adamu Tefera. Source: A.Tefera

Dr Fisaha Haile Tesfay. Source: FH.Tesfay

Ayalew Hundessa. Source: A.Hundessa
“ሰላም ለማምጣት ከተፈለገ መሪዎች በቀጥታ መነጋገር አለባቸው። ወደዚያ የሚያሸጋግሩ የተመቻቹ ሁኔታዎች መፈጠር አለባቸው። አገራዊ መፍትሔ መፈለግ አለበት።” አቶ አዳሙ ተፈራ
“በጦርነት በፍጹም የትም አይደረሰም። የሰላም ድርድሩ የእውነት ከሆነ፤ አገሪቷ አሁን ካለችበት ምስቅልቅል ሁኔታ ወጥታ እንድትገኝ የምንፈልግ ከሆነ የፌዴራል መንግሥቱ ወይም የዐቢይ መንግሥት ላይ ተፅ ዕኖ ማሳደር ያስፈልጋል።” ዶ/ር ፍሳሃ ኃይለ ተስፋይ