ፍቅር ይጣፍጣል። ጣዕሙ ይበልጥ ልብ ላይ ነው የሚሰማው። በቀላሉ የማይታይ፤ ነፍስን ገዝቶ የሚሞላ። አንተን በመውደዴ ሁሉ ነገሬ ተቀየረ። ማታ እስከማገኝህ እጓጓለሁ። በዕቅፍህ ውስጥ ስኖር እረጋጋለሁ። በሕይወታችን ውስጥ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ባይሆንም ስለማፈቅርህ ትዕግስተኛ ሆኛለሁ። አከብርሃለሁ። ዘላለሜን አፈቅርሃለሁ። Happy Valentine's Day!ቲና ለብሩክ (ከፐርዝ)
የልጆቼ እናት ውዷ ባለቤቴ፤ 'ውዴ' ስልሽ ያንስብኛል። አንቺ ልዩ፣ ጣፋጭና ተፈቃሪ ነሽ። ልብሽ ሩህሩህ ነው። ጓደኞቼ 'ምን ዓይነት ዕድለኛ ነህ?' ይሉኛል። ዓመታቶች ቢያልፉም፤ ሁልጊዜም ፍቅራችን አዲስና ጣፋጭ ነው። አይሰለችም። እንኳን ለቫላንታይን ቀን አደረሰሽ! በፍቅርሽ እንደተሸነፍኩ ለዘላለሙ እኖራለሁ።ፈይሳ ቱሉ ለሐዊ መገርሳ (ከአደላይድ)
የኔ ፍቅር፤ ስለ አንቺ ሳስብ የሚሰማኝን ስሜት ለመግለፅ ቃላት እያጣሁ ነው። ከአወቅኩሽ ቀን ጀምሮ ልዩ የሆነች ሚስት እንዳገኘሁ ልቤ ይነግረኝ ነበር። ደስታና ፍቅርን ወደ ሕይወቴ አምጥተሻል። አንቺ የሕይወቴ፣ የልቤና የነፍሴ ዋና አካል ነሽ። ምርጥ ዕጣ ክፍሌ ስለሆንሽ አመሰግናለሁ። የሰጠሁሽ ልቤ ውስጥ አኖርሻለሁ። ሁልጊዜም አፈቅርሻለሁ። Happy Valentine's Day!ልቡ ከሜልበርን ለጊፍቲ አዲስ አበባ





