አንኳሮች
- የእንግሊዝ ንጉሥ የአውስትራሊያም ርዕሰ ብሔር ናቸው
- ሁሉም የጋራ ብልፅግና አገራት ሉዓላዊ አገራት ናቸው
- ንጉሡ በቀጥታ የዕለት - ተዕለት አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ አይገቡም
- የአውስትራሊያ ሪፕብሊካውያን ንቅናቄ አውስትራሊያውያን የራሳቸውን ርዕሰ ብሔር ሊመርጡ ይገባል ብሎ ያምናል
“አውስትራሊያ የተመሠረተችው የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ሆና በመሆኑ በርካታ የእንግሊዝ ልማዶችን ተውሳለች ወይም አዋድዳ ይዛለች” ሲሉ የአውስትራሊያ ዲሞክራሲ ሙዚየም ተመራማሪ ካምፕቤል ሮድስ ይናገራሉ። “ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ዘውዳዊ አገዛዝ ነው” ሲሉም አክለው ያስረዳሉ። በመሆኑም፤ የአገረ እንግሊዝ ንጉሥ የአውስትራሊያም ርዕሰ ብሔር ናቸው።
ኤልሳቤጥ አሌግዛንድራ ሜሪ ዊንድዘር ከወርኅ ፌብሪዋሪ 1952 አንስቶ የአገረ እንግሊዝና 14 የጋራ ብልፅግና አገረ ግዛቶች ንግሥት ሆነው ገዝተዋል። .
ዳግማዊት ኤልሳቤጥ በእንግሊዝ የዘውድ አገዛዝ ታሪክ ውስጥ ለረጅም ጊዜያት የገዙ ንግሥት ናቸው። ሕልፈተ ሕይወታቸውን ተከትሎም ልጃቸው ቻርልስ ንጉሥ ሆነዋል። ንግሥናቸውም የተሰየመው ንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ ተብሎ ነው።
ሁሉም የጋራ ብልፅግና አገራት የራሳቸው ሕጎችና መንግሥታት ያላቸው ሉዓላዊ አገራት ናቸው።
የአውስትራሊያ ሪፐብሊክ ንቅናቄ አገር አቀፍ ዳይሬክተር ሳንዲ ቢያር የአውስትራሊያ መንግሥት መዋቅርና ስልጣናት ከአውስትራሊያ ሕገ መንግሥት የመነጩ እንደሆነ ሲገልጡ፤ .
“አውስትራሊያ ሌሎች ሁሉም ሕጎች የሚገዙበት በፅሁፍ የሠፈረ ሕገ መንግሥት አላት፤ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ዋነኛ ገዲብ ሰው የእኛ ርዕሰ ብሔር የእንግሊዝ ንግሥት ወይም ንጉሥ ነው። የርዕሰ ብሔራችን ነዋሪነት ከሌላኛው ዓለም ጫፍ በመሆኑ ጠቅላይ እንደራሴው በእነሱ ስም የአውስትራሊያ ተወካይ ይሆናል” ብለዋል።

With the death of Queen Elizabeth II, her son Charles became King. He has begun his reign as King Charles III. Credit: Carl Court/AP/AAP Image
ዘውደኛው የእኛ ርዕሰ ብሔር ነው፤ ስለሆነም አውስትራሊያ በ 'ሕገ መንግሥታዊ የዘውድ ሥርዓትነት' ትጠቀሳለች።
ጁዲት ብሬት በላትሮብ ዩኒቨርሲቲ ጡረተኛ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ናቸው። የርዕሰ ብሔሩ ስልጣን ከምልክትነት ያለፈ አለመሆኑን ሲያመላክቱ፤
“የሥራ አስፈፃሚ ስልጣን የላቸውም። የሥራ አስፈፃሚ ስልጣን ያለው ርዕሰ መንግሥቱ ነው። እናም፤ ለአገሪቷ አንድነት ምልክታዊ በሆነው ርዕሰ ብሔርና ለምርጫ ውድድር ክፍት በሆነው ርዕሰ መንግሥት መካከል ልዩነት አለ” ሲሉ ተናግረዋል።
ንጉሡ የአውስትራሊያ የዕለት - ተዕለት አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ አይገቡም፤ በአገሪቱ ሕብረተሰብ፣ ምጣኔ ሃብት ወይም መንግሥት ውስጥ ቀጥተኛ የሆነ ተፅዕኖ የላቸውም።
ይሁንና የአውስትራሊያ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጥልቅ ወቅታዊ ገለጣዎች ይደረግላቸዋል፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩም እንደ አማካሪና ምስጢረኛ ይሆናሉ።
የጠቅላይ እንደራሴው ሚና ምንድነው?
ንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ ካንብራ ላይ በጠቅላይ እንደራሴ እንዲሁም በየክፍለ አገራቱ መዲናዎች በእንደራሴዎች ይወከላሉ። .
የጠቅላይ እንደራሴ ውክልና የሚቸረው በአውስትራሊያ መንግሥት አማካሪነት በንግሥት ወይም በንጉሥ ነው። የወቅቱ ጠቅላይ እንደራሴ የተከበሩ ዴቪድ ሃርሌይ ናቸው።
እንደ ንጉሡ ሁሉ ጠቅላይ እንደራሴውም በመንግሥት የዕለት - ተዕለት ክንዋኔዎች ውስጥ ጣልቃ ባይገቡም ሁነኛ ኃላፊነቶች ያላቸው መሆኑን ሳንዲ ቢያር ሲያመላክቱ፤
በየጊዜው ሕግ በፓርላማ ሲያልፍ ወይም ወደ ምርጫ ስናመራ... [የንጉሡን] ተወካይ ይሁንታ ይሻል።ሳንዲ ቢያር፤ የአውስትራሊያ ሪፐብሊክ ንቅናቄ አገር አቀፍ ዳይሬክተር
አውስትራሊያ ውስጥ የዘውድ ተወካዩ የጠቅላይ ሚኒስትር ስያሜን ይሁንታ ይቸራል “ሁሌም ባይሆን፤ በአብዛኛው በተካሔደው ምርጫ አብላጫ የፓርላማ ወንበሮችን ካሸነፈው ፓርቲ”

Queen Elizabeth II watches Tjapukai Aboriginal ceremonial fire performance near Cairns, 2002. Credit: Torsten Blackwood/AFP via Getty Images
ቁርኝትን ብጠሳ
በ1986ቱ የአውስራሊያ ድንጋጌ ከዘውዱ ባሻገር በእንግሊዝና አውስትራሊያ መካከል የነበሩት ይፋዊ ትስስሮሽ ተቋርጠዋል።
አያሌ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች ዘውዳቂ ቁርኝታቸውን በጥሰዋል። በቅርቡም ባርቤዶስ ተለይታለች። የአሥራ አምስት የጋራ ብልፅግና አገረ ግዛቶች ትስስሮሽ ግና ቀጥሎ አለ።
አውስትራሊያ ውስጥም ለመጀመሪያ ጊዜ የሌበር መንግሥት ማት ቲስትሌዝዊይትን የሪፐብሊክ ሚኒስትር ደኤታ አድርጎ ሾሟል።
በአውስትራሊያውያን ዘንድም የሪፐብሊክ ስሜት የማደሩ መጠን እየጨመረ መጥቷል። ይህንኑ መንፈስ ተከትሎም ሳንዲ ቢያርና የአውስትራሊያ ሪፐብሊክ ንቅናቄ የለውጥ ግፊታቸውን ቀጥለዋል።
የአውስትራሊያ ሪፐብሊክ ንቅናቄ የእንግሊዝን ንግሥት ወይም ንጉሥ የአገራችን ርዕሰ ብሔር ከማድረግ ይልቅ በአውስትራሊያውያን የተመረጠ አውስትራሊያዊ ሊኖረን ይገባል።ሳንዲ ቢያር፤ የአውስትራሊያ ሪፐብሊክ ንቅናቄ ዳይሬክተር
"በዚህ እናምናለን፤ ስለምን እንደ እኛ ባለ ነፃ አገር ውሳኔዎች ሁሉ የአውስትራሊያን ጥቅሞች በሚያስጠብቁ የእኛ ተወካዮች መሆኑ ትርጉም ያለው ነው” ሲሉ ሳንዲ ቢያር ተናግረዋል።
ጁዲት ብሬትም በበኩላቸው፤ ለእንግሊዝ ዘውዳዊ ሥርዓት ያለው ስሜታዊነት እየተለወጠ መሆኑን አመላክተዋል።
ባለፉት አሠርት ዓመታት ዝነኛ የዘውዳዊ ቤተሰብ አባላት ፍጥነት የታከለበት የአውስትራሊያ ጉብኝቶች ተከታታይነትም በበኩሉ ግለቱን እንዲቀንስ ማድረጉን ገልጠዋል።

The Duke and Duchess of Cambridge visit Taronga Zoo, Sydney during their official 2014 tour to New Zealand and Australia Credit: Anthony Devlin/PA Images via Getty Images
የሪፐብሊካን ንቅናቄ በበርካታ አገራት ስር እየሰደደ መሔድን ልብ ያሉት ንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ በቅርቡ ሩዋንዳ ውስጥ በተካሔደው የጋራ ብልፅግና ርዕሰ መንግሥታት ስብሰባ ላይ የለውጥ ሂደትን የተገነዘቡ መሆኑን አስመልክተው ሲናገሩ፤ አንድ ሶስተኛ ሰብዓዊ ፍጡራንን የሚወክሉ ሁሌም "ነፃ ሆነው የቆሙ፣ ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ የነፃ ማኅበር" ወካዮች መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል።
አክለውም "ቀደም ሲል አንዳልኩት ሁሉ፤ አሁንም ግልፅ ሆኜ መናገር እሻለሁ። እንደ ሪፕብሊክ ወይም ዘውዳዊ ሕገ መንግሥትን የተከተለ ሕገ መንግሥታዊ አባልነትን እያንዳንዱ አባል አገር የሚወስነው ይሆናል" ሲሉ ታዳሚ የነበሩት ፕሬዚደንቶችና ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ልብ አሰኝተዋል።
ባለፈው ዓመት የአውስትራሊያ ሪፐብሊክ ንቅናቄ ከ 8,000 በላይ አውስትራሊያውያንን የአውስትራሊያ ሪፐብሊክ ምን ኢመስል እንደሚችል ግንዛቤን እንዲጨብጡ የአውስትራሊያውያን ምርጫ ሞዴል ን በጃኑዋሪ 2022 ይፋ አድርጓል። የአውስትራሊያ ሕገ መንግሥትን በማሻሻል አውስትራሊያውያን የራሳቸውን ርዕሰ ብሔር ለመምረጥ ምን ዓይነት ለውጦችን መከወን እንደሚያሻ አስፍሯል።