Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

“የቶረስ ስትሬት ደሴት ነዋሪዎች ባንዲራ፡ መሬት፣ ባሕር እና ሕዝብ”

Australia Explained – Torres Strait flag
The visibility of the flag can be powerful for Torres Strait Islander people. Credit: Kelly Defina/AFL Photos/via Getty Images

አውስትራሊያ ውስጥ፣ ሶስት ባንዲራዎች ሲውለበለቡ ሊያዩ ይችላሉ፡ የአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንዲራ፣ የአቦርጂናል ባንድ እና የቶረስ ስትሬት አይላንደር ባንዲራ።የአቦርጂናል እና የቶረስ ስትሬት አይላንደር ሕዝቦች በአውስትራሊያ ሁለት የተለያዩ ነባር ሕዝቦች ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም የራሳቸው ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ እና ባንዲራ አላቸው። ለአብዛኛዎቹ የቶረስ ስትሬት አይላንደር ሰዎች ይህ ባንዲራ ለማንነታቸው እና ለህልውናቸው ታልቅ ስፍራን የሚሰጡት ነው፡ በደሴቶች ላይ ሆነ በዋናው መሬት ወይም በውጭ ቢኖሩ ይህ የማይለወጥ ነው፡፡


Published

Updated

By Nikyah Hutchings

Presented by Martha Tsegaw

Source: SBS




Share this with family and friends


አውስትራሊያ ውስጥ፣ ሶስት ባንዲራዎች ሲውለበለቡ ሊያዩ ይችላሉ፡ የአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንዲራ፣ የአቦርጂናል ባንድ እና የቶረስ ስትሬት አይላንደር ባንዲራ።የአቦርጂናል እና የቶረስ ስትሬት አይላንደር ሕዝቦች በአውስትራሊያ ሁለት የተለያዩ ነባር ሕዝቦች ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም የራሳቸው ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ እና ባንዲራ አላቸው። ለአብዛኛዎቹ የቶረስ ስትሬት አይላንደር ሰዎች ይህ ባንዲራ ለማንነታቸው እና ለህልውናቸው ታልቅ ስፍራን የሚሰጡት ነው፡ በደሴቶች ላይ ሆነ በዋናው መሬት ወይም በውጭ ቢኖሩ ይህ የማይለወጥ ነው፡፡


አንኳሮች

  • የቶረስ ስትሬት አይላንደር ባንዲራ መሬትን፣ ባሕርን እና ሕዝብን ይወክላል።
  • ይህ ባንዲራ በ1992 በቶረስ ስትሬት አይላንደር አርቲስት አንክል በርናርድ ናሞክ ሲኒየር ተነድፎ የተፈጠረ ሲሆን አሁን ከአውስትራሊያ ሶስት ብሔራዊ ባንዲራዎች አንዱ ነው።
  • አረንጓዴ፣ ሰማያዊ፣ ጥቁር እና ነጭ ቀለሞቹ ውስጥ የዳሪ (ባህላዊ የራስ ማጌጫ) እና አምስት ነጥብ ያለው ኮከብ አለ፣ ይህም የቶረስ ስትሬት አምስት ዋና ደሴቶችን ቡድኖችን ይወክላል።
  • ለብዙ ሰዎች ይህ ባንድ የማንነት፣ የኩራት እና የህልውና ምልክት ነው፤ አሁንም በዓለም ዙሪያ ይታያል።

    የቶረስ ስትሬት አይላንደር ባንዲራ ከየት መጣ?

    የቶረስ ስትሬት ደሴቶች በኩዊንስላንድ የኬፕ ዮርክ ጫፍ እና በፓፑዋ ኒው ጊኒ መካከል የሚገኙ ደሴቶች ናቸው። እነዚህ ደሴቶችም እንደሚከተለው ይታወቃሉ ፦

    • ሰሜናዊ ክፍል (Boigu, Dauan, Saibai)
    • ምሥራቃዊ ደሴቶች (Erub, Mer, Ugar)
    • ምዕራባዊ ክፍል (St Pauls, Kubin, Badu, Mabuiag)
    • መካከለኛ ክፍል (Masig, Poruma, Warraber, Iama)
    • ደቡባዊ ክፍል (Thursday Island, Horn Island, Prince of Wales እና Hammond Islands, NPA እና ዋና መሬት አውስትራሊያ)

    በ1992 ዓ.ም. የደሴቶች አስተባባሪ ምክር ቤት የቶረስ ስትሬት ደሴቶች ነዋሪዎች ለማህበረሰቡ ባንዲራ ንድፍ እንዲያቀርቡ ውድድር አዘጋጀ። የአሸናፊው ንድፍ አንክል በርናርድ ናሞክ Uncle Bernard Namok ከThursday Island ነበር።

    የታላቁ በርናርድ ልጅ፣ በርናርድ ናሞክ ጁኒየር፣ አባቱ ለዚህ ውድድር ባንዲራውን በThursday Island ቤታቸው የማእድ ቢት ጠረጴዛ ላይ ሆኖ ሲሰራ ማየቱን ያስታውሳል፤ በሌሊት ንድፎችን ሲሳል ይመለከት ነበር።

    አንክል በርናርድ (Uncle Bernard) የራሱ ንድፍ የሕዝቡ መለያ ምልክት ሆኖ ሲጸድቅ ለማየት አልቻለም፤ የባንዲራው ውድድር ከተጠናቀቀ ብዙም ሳይቆይ አረፈ።

    ለበርናርድ ጁኒየር፣ ይህ ባንዲራ ከአባቱ ጋር ያለውን ትስስር በሕይወት ያቆየዋል፤ አባቱ ማታ ማታ ተቀምጦ ባንዲራውን ሲሳል ይመለከተው የነበረውን ጊዜም ያስታውሰዋል።

    Australia Explained - Torres Strait flag
    The Australian, Indigenous and Torres Strait Islands flags fly together in front of the High Court of Australia in Canberra. Credit: AAP Image/Lukas Coch

    የቶረስ ስትሬት ደሴቶች ባንዲራ ትርጓሜው ምንደን ነው ?

    በባንዲራው ላይ ያሉት ቀለሞችና ምልክቶች እያንዳንዳቸው የተለየ ትርጉም አላቸው፦

    • አረንጓዴ መሬቱን ይወክላል።
    • ሰማያዊ የቶረስ ስትሬትን ውሃዎች ይወክላል።
    • ጥቁር የቶረስ ስትሬት ደሴቶችን ይወክላል።
    • ነጩ ዳሪ (ባህላዊ የራስ ልብስ) የቶረስ ስትሬት ደሴቶችን ባህላዊ ማንነት መለያ ነው።
    • አምስቱ ነጫጭ ኮከቦች በቶረስ ስትሬት ያሉትን አምስቱን ዋና ዋና የደሴት ቡድኖች ይወክላሉ።

    የአቦርጂናል ባንድ እና የቶረስ ስትሬት አይላንደር የሕግ ተማሪ ታይሬል ቪቲ ፤ ተወልዶ ያደገው በተረስዴይ ደሴት ሲሆን በአሁን ሰአትም የሚኖረው ታውንስቪል ኩዊንስላንድ ነው ።

    እሱ እንደሚለውም ባንዲራው የሕዝቡን ማንነት፣ ታሪክ እና ጽናትን ይወክላል።

    Australia Explained - Torres Strait flag
    Seeing the flag in public arenas creates a sense of recognition and inclusion. Credit: AAP Image/Lukas Coch

    ባንዲራውን እያዪ ማደግ ምን አይነት ስሜትን ይፈጥራል ?

    በርናርድ ጁኒየር እና ታይሬል ሁለቱም በተርስዴይ ደሴት (Thursday Island) ላይ አድገዋል። ደሴቴ ትንሽ ቢሆንም የተለያዪ እንቅስቃሴዎች የሚካሄድበት ፣ በቤተሰብ እና በባህል የተሞላ ማህበረሰብ ነው ሲሉ ይገልጹታ።

    ለታይሬል ደግሞ ባንዲራው የዕለት ተዕለት ሕይወቱ አካል ነው።

    “ባንዲራችንን እንደ ፍርድ ቤቶች እና በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሳየው፣ ከዋናው መሬት ርቃ ከምትገኝ ትንሽ ደሴት የመጣሁ ቢሆንም ስፍራዋ ጎልታ መታየቷ ክብር እንዲሰማኝ ያደርገኛል። ወደ ዋናው መሬት ስገባ ባንዲራችንን በፍርድ ቤት፣ በአካባቢዎ የፖስታ ቤት ወይም ሰዎች በልብሳቸው ላይ ለብሰው ሳየው፣ እዚህ በዋናው መሬት ያሉ ሰዎች በደሴቶቹ ላለነው ሕዝብ ብዙ ፍቅርና ክብር እንዳላቸው ይሰማኛል።

    “ይህ ሁላችንም የአውስትራሊያ አካል መሆናችንን፣ እንዲሁም እንደ አንድ ሕዝብ በአንድነት ወደፊት ለመራመድ የምንችል መሆናችንን ያሳየኛል ።

    ”በርናርድ ጁኒየር ባንዲራው በየቦታው ከመታየቱ በፊት የነበረውን ዘመን ያስታውሳል። በ1990ዎቹ የባንዲራው ውድድር ከተካሄደ በኋላ ባንዲራው በደሴቶቹ ሁሉ በቀስታ ሲስፋፋም ተመልክቷል፣ አሁን ግን በፍጹም አይታይም ብሎ ባሰበባቸው ቦታዎችም እንኳን እየታየ እንደሆነ ይናገራል።

    ባንዲራውን የት እናያለን?

    ዛሬ የቶሬስ ስትሬት ደሴተኞች ባንዲራን በመላው አውስትራሊያ ይውለበለባል። ከአቦሪጂናል ባንዲራና ከአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንዲራ ጎን ለጎን በትምህርት ቤቶች፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በፓርላማዎች፣ በአካባቢ ምክር ቤቶች እና በፍርድ ቤቶች ላይ ሊያዩት ይችላሉ።

    ለታይሬል ይህ ትልቅ ትርጉም አለው። ባንዲራውን በፍርድ ቤቶች፣ በፖስታ ቤቶች እና ሰዎች በልብሳቸው ላይ ሲያይ፣ እንደሚታወቅ፣ እንደሚከበር እና የማህበረሰቡ አካል እንደሆነ ያሰማዋል።

    Australia Explained – Torres Strait flag
    The flag is a powerful symbol of identity and belonging on the islands, the mainland and overseas. Credit: Danny Lawson/PA/Alamy/AAP Image

    በርናርድ ጁኒየርም የቶሬስ ስትሬት ደሴተኞች ባንዲራ ከቤቱ በጣም ርቀው ባሉ ቦታዎችም ሲውለበለብ ተመልክቷል። የእሱን ዶክመንተሪ "Carrying The Flag" ይዞ በውጭ አገሮች በተዘጋጁ ፌስቲቫሎች ላይ ተሳትፏል፣ እንዲሁም ባንዲራውን በአውስትራሊያ ኤምባሲዎች በለንደን፣ በፓሪስ እና በኒው ዮርክ ሲውለበለብ አይቷል።

    በርናርድ ጁኒየር በየጊዜው ባንዲራውን ሲያይ፣ ወደ ልጅነቱ ዘመን በተርስዴይ ደሴት ያሳለፈውን ሕይወት እንደሚመለስበት ይናገራል።

    “የትም ቦታ ብሆን፣ ባንዲራውን ባየሁ ጊዜ በደሴቱ ላይ ያሳለፍኩት የልጅነት ዘመኔ ይታወሰኛል። እንዲሁም ከአባቴ ትከሻ ላይ ሆኜ እነዚያን ሁሉ ስዕሎች ሲስል እያየሁ ያሳለፍኩት ጊዜ ወደ አእምሮዬ ይመጣል።”

    ባንዲራው ለቀጣዩ የያዘው ተምሳሌት ምንድን ነው ?

    በርናርድ ጁኒየር ልጆች ስለ ቶሬስ ስትሬት ደሴተኞች ባንዲራ እናከጀርባው ያለውን ታሪክ እያወቁ እንዲያድጉ ይፈልጋል። እርሱ ከቶማስ ማዮ (Thomas Mayo) ጋር በመተባበር "Our Flag, Our Story" የተሰኘውን የልጆች መጽሐፍ የጻፈ፣ ሥዕሎቹም በቶሪ-ጄይ ሞርዴይ (Tori-Jay Mordey) የተሰሩ ናቸው።

    በርናርድ ጁኒየር ስለ "Our Flag, Our Story" ያለውን አስፈላጊነት እንዲህ ይገልጻል፦

    “በተለይም በReconciliation Week እና NAIDOC Week ወቅት በብዙ ትምህርት ቤቶች መጽሐፉን ለልጆች አንብቤ አቅርቤዋለሁ። ከመምህራንና ከትምህርት ቤት ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የምሰማው አስተያየት አንድ ነው፤ ልጆቹ መጽሐፉን ማንበብ በጣም ይወዳሉ።”

    Tyrell Viti graduation.JPG
    "It's good that we have a flag dedicated and designed by us, for us," Tyrell Viti says. Source: Supplied / Tyrell Viti

    ታይሬል እንደሚሉት ከሆነም “ለእኛ በእኛው የተነደፈና እኛን የሚወክል ባንዲራ ስላለን በጣም ጥሩ ነው። ይህ ጉዟችንን እንድንቀጥል፣ ወደፊትም እንድንራመድ ያነሳሳናል። እንዲሁም በባህላዊ ማንነታችን እንድንኮራና እንድንታወቅ ያደርገናል። ”የቶሬስ ስትሬት ደሴተኞችን ባንዲራ በምታዩበት ጊዜ፣ መሬትን፣ ባሕርን እና ሕዝቡን የሚወክል ሕያው ምልክትን እያያችሁ ነው። እንዲሁም በቶሬስ ስትሬት ደሴቶች፣ በመላው አውስትራሊያ እና በዓለም ዙሪያ ዛሬም ድረስ በሕይወት ያሉና የሚቀጥሉ ባህሎችን ይወክላል።

      Subscribe to or follow the Australia Explained podcast for more valuable information and tips about settling into your new life in Australia.

      Do you have any questions or topic ideas? Email australiaexplained@sbs.com.au

      በአውስትራሊያ ሕይወትዎን በተሻለ ሁኔታ ለመጀመር የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችንና ምክሮችን ለማግኘት፣ Australia Explained ፖድካስትን (Subscribe) ያድርጉ ውይም ድረ- ገጻችንን ይከተሉ (Follow)።

      ጥያቄ ወይም ሊብራራ የሚገባ ሀሳብ አለዎት? ወደ australiaexplained@sbs.com.au ኢሜይል ይላኩ።


      Latest podcast episodes

      Follow SBS Amharic

      Download our apps

      Watch on SBS

      SBS World News

      Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

      Stream now