Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE starting June 12 2026

የአውስትራሊያ ነባር ዜጎችን የመሬት መብቶች መገንዘብ

WAVE HILL WALK OFF 50TH ANNIVERSARY

Several thousand marchers celebrate the 50th anniversary Wave Hill Walk-off in Kalkarindji on Friday August 19, 2016. On August 22 1966 Vincent Lingiari led several hundred Gurindji people off Wave Hill Station in a protest to gain fair wages, which morphed into the battle for land rights, which took nine years to eventuate. Credit: AAP Image/Neda Vanovac

ምናልባትም "የምንፈልገው ምንድን ነው? የመሬት መብቶች!" የሚል የተቃውሞ ሠልፍ መፈክር ሰምተው ይሆናል፤ ግና በእርግጥ ምን ማለት ነው? መሬት የአቦርጂናል እና ቶረስ መሽመጥ ደሴት የማንነት፣ ባሕልና ደህንነት ማዕከል ነው። "ሀገር" በሚል ዕሳቤ የሚታወቀው አባባል መሬት፣ የውኃ መስመሮች፣ ሰማይ እና ሕይወት ያላቸውን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው። በእዚህ አውስትራሊያ ስትገለጥ ክፍለ ዝግጅት፤ የነባር ዜጎች የመሬት መብቶች ምንን እንደሚያካትቱ፣ የትኛውን መሬት እንደሚሸፍን፣ ማን የባለቤትነት ይገባኛልን ማንሳት እንደሚችል እና በነባር ዜጎች ማኅበረሰባት ላይ ስላለው ተፅዕኖ እንዳስሳለን።


Published

Updated

By Nikyah Hutchings

Source: SBS



Share this with family and friends


ምናልባትም "የምንፈልገው ምንድን ነው? የመሬት መብቶች!" የሚል የተቃውሞ ሠልፍ መፈክር ሰምተው ይሆናል፤ ግና በእርግጥ ምን ማለት ነው? መሬት የአቦርጂናል እና ቶረስ መሽመጥ ደሴት የማንነት፣ ባሕልና ደህንነት ማዕከል ነው። "ሀገር" በሚል ዕሳቤ የሚታወቀው አባባል መሬት፣ የውኃ መስመሮች፣ ሰማይ እና ሕይወት ያላቸውን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው። በእዚህ አውስትራሊያ ስትገለጥ ክፍለ ዝግጅት፤ የነባር ዜጎች የመሬት መብቶች ምንን እንደሚያካትቱ፣ የትኛውን መሬት እንደሚሸፍን፣ ማን የባለቤትነት ይገባኛልን ማንሳት እንደሚችል እና በነባር ዜጎች ማኅበረሰባት ላይ ስላለው ተፅዕኖ እንዳስሳለን።


አንኳር ነጥቦች

  • የመሬት መብት ለአቦርጂናል እና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ማኅበረሰባት ለባሕላዊ፣ ማሕበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ትሩፋት የግል ንብረቶችን ሳይሆን የተወሰነ ዘውድ መሬት።
  • የመሬት መብቶች፣ የሀገር በቀል ይገባኛልነት እና የቃል ኪዳን ውል ሕጋዊና ፖለቲካዊ ሂደታቸው ለየቅል ነው፤ ሆኖም የሁሉም ትልም ነባር ዜጎች ከምድራቸው ጋር ያላቸን ቁርኝትና ራስን በራስ የማስተዳደር ዕውቅና ማስገኘት ማስቻል ነው።
  • ንቅናቄው የተጀመረው የ1966ቱን Wave Hill Walk-Off ከመሰሉቱ ኩነቶች ሲሆን፤ የአቦርጂናል የመሬት መብቶች (ሰሜናዊ ግዛት) ወደ መሰለ የ1975ቱ ድንጋጌ አምርቷል፤ ምንም እንኳ አሁንም ድረስ በሂደት ላይ ያለ ቢሆንም።

የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የመሬት መብቶች ምንድን ናቸው?

ለአያሌ ዓመታት፤ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ከመሬታቸው ጋር ያላቸው ቁርኝት ዕውቅና አልተቸረውም። በባሕላዊ መሬቶቻቸው ላይ የበላይነት እንዲኖራቸው የመሬት መብቶች ሕግ ተቀርጿል።

ከቅኝ አገዛዝ በፊት፤ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች በአሥር ሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት መሬታቸውን ተከባክበዋል።

ይሁንና ቅኝ አገዝዛ "ባለቤት አልባ መሬት" በሚል ሐሰተኛ አስባብ ያለ አንዳች ስምምነት መሬታቸውን ነጥቋል።

Gough Whitlam, Wave Hill Walk Off, Vincent Lingiari
Prime Minister Gough Whitlam symbolically returning land to the Gurindji people on 16 August 1975, an act famously represented by Whitlam pouring sand into Vincent Lingiari's hand. Source: AAP

የነባር ዜጎች የመሬት መብቶች ንቅናቄ አጀማመር እንደምን ነው?

የዘመናዊ የመሬት መብት ንቅናቄ የተጀመረው በጉሪንጂ ስቶክሜን እና የሰሜናዊ ግዛት ቤተሰቦች በ1966 Wave Hill Walk-Off ነው። ተቃውሞው ክብካቤ የጎደለው የሥራ ሁኔታዎችን አመላክቷል፤ ልማዳዊ የመሬት ባለቤትነት እንዲመለስ ጠይቋል።

በ1967 የተካሔደው ሕዝበ ውሳኔ የአውስትራሊያ መንግሥት የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ሕግ እንዲያወጣ ስልጣን ሰጥቷል። ይህም ለመጀመሪያ ጊዜ ለልማዳዊ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ሰጪ ለሆነው የ1976ቱ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ (ሰሜናዊ ግዛት) ድንጋጌ መንገድ ጠርጓል።

የተወሰኑ ክፍለ ሀገራት እና ግዛቶች የየራሳቸው የመሬት መብቶች ድንጋጌ አሏቸው፤ ሆኖም አውስትራሊያ አንድ ወጥ ብሔራዊ የመሬት መብቶች ሕግ የላትም።

የነባር ዜጎች የመሬት መብት የሚሸፍነው ምንድን ነው?

የመሬት መብት የሚመለከተው የግል ንብረትን ሳይሆን፤ የዘውድ መሬት በመባል የሚታወቀውን በመንግሥት ተይዞ ያለውን መሬት ነው። ተመላሽ መሬቱም ለሽያጭ ወይም ሞርጌጅነት አይውልም። ይልቁንም፤ የነባር ዜጎች ማኅበረሰባት የበላይ ጠባቂነት እንዲከባከቡትና ውሳኔዎችንም እንዲሰጡበት አስቻይ ነው።

የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ተመላሽ መሬቱን ለማስተዳደርና ውክልናንም ለመቸር የመሬት ምክር ቤቶች ተቋቁመዋል። ምክር ቤቶቹም ማኅበረሰባቸው መሬቱን ለባሕላዊ፣ ማኅበራዊ፣ የተፈጥሮ ጥበቃና ምጣኔ ሃብታዊ ዓላማዎች እንዲጠቀሙበት እገዛን ይቸራሉ።

በአቦርጂናል የመሬት መብቶች፣ ሀገር በቀል ባለቤትነትና የቃልኪዳን ውል መካከል ያሉ ልዩነቶች ምንድን ናቸው?

ምንም እንኳ ቃሎቹ ተዘውትረው አንድ ላይ ቢነሱም፤ ትርጓሜዎቻቸው ለየቅል ናቸው፤

  • የመሬት መብቶች፤ በመንግሥታት የተቀረፁ ሕጎች የተወሰኑ አካባቢዎች የዘውድ መሬትን ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች እንዲመለሱ የሚያስመልሱ ሲሆን፤ በአብዛኛው የሚተዳደሩትም በመሬት ምክር ቤቶች ነው።  
  • ሀገር በቀል ባለቤትነት፤ የተወሰኑ ነባር ዜጎች አሁንም ድረስ በባሕላዊና ልማዳዊ ሕጎች መሠረት ይዘዋቸው ያሉ የመሬትና ውኃዎቻችው ባለ መብትነት ሕጋዊ ዕውቅና አላቸው።
  • የቃል ኪዳን ውል፤ በነባር ዜጎችና መንግሥታት መካከል የተከወነ መደበኛ ስምምነት። እንደ ኒውዝላንድና ካናዳን የመሳሰሉ ሀገራት የቃል ኪዳን ውሎች ያሏቸው ሲሆን፤ አውስትራሊያ ግ ና እስካሁንም ድረስ አገር አቀፍ ውል የላትም።

እኒህ አሠራሮች በጋራ ፍትሕን፣ ዕውቅናንና ራስን በራስ ማስተዳደርን ለነባር ዜጎች ለማስፈን ያለሙ ናቸው።

wave hill sign.png
The Wave Hill walk-off, led by Vincent Lingiari, was a pivotal moment in Australian Aboriginal land rights history. In 1966, Gurindji stockmen, domestic workers, and their families walked off Wave Hill Station in protest against poor working conditions and a lack of land rights. Credit: National Museum Australia

የነባር ዜጎች የመሬት መብት በአሁኑ ወቅት ምን ፋይዳ አለው?

ተመላሽ መሬት ማኅበረሰባት ከቋንቋቸው፣ ባሕልና ቀዬአቸው ጋር ዳግም እንዲቆራኙ ያግዛል። እንዲሁም፤ በቤት፣ ጤና፣ ትምህርትና ምጣኔ ሃብት ራስን ለመቻል ይረዳል።

የዊራንጁሪ ንዬምባዋ ሴትና የውኃ መብቶች ተጠባቢዋ ዶ/ር ቨርጂኒያ ማርሻል፤ በተለያየ ገፅታ ሲያስረዱ፤

“ውኃው እኛን ያናግረናል ወይም ዛፎች እኛን ያናግሩናል፤ ይሁንና የምዕራባውያንን የተፈጥሮ ርዕዮተ ዓለም መውሰድ አያሻንም… ሕጋችንና የትርክት ቀረፃችን ለግንዛቤያችን አመላካች ይሆኑናል” ብለዋል።

የመሬት መብቶች የአንድን ግለሰብ ንብረት ወይም ጓሮ ነጣቂ አይደሉም። ትኩረታቸው ተመላሽ የዘውድ መሬት የተወሰኑ አካባቢያዎች ታሪካዊ ወይም ባሕላዊ ቁርኝት እንዳላቸው ዕውቅናን ስለ መላበሳቸው ነው።

የቀዬ አብነት፤ ዳርኪንጃንግ የመሬት ምክር ቤት

የዳርኪንጃንግ የአቦርጂናል መሬት ምክር ቤት የተመሠረተው በኒው ሳውዝ ዌይልስ የአቦርጂናል መሬት መብቶች ድንጋጌ መሠረትነት ሲሆን፤ የመሬት መብቶች ትግበራን በድርጊት ያሳየ ነው።

የጎሜሮዩ ሰውና ከምክር ቤቱ መሥራቾች አንዱ የሆኑት አጎት ባሪ ዳንከን በ1983 እንደምን እሳቸው ጓሮ እንደተጀመረ አውስተው ሲያነሱ፤

“ይህን ማኅበረሰብ አንድ ላይ አሰባስቧል። መሬትን ለሙዋዕለ ንዋይ አውሎ መልሶ ወደ አቦርጂኖች ባለቤትነት የማምጫ መንገድ ነበር” ብለዋል።

በዓመታት ውስጥ፤ ዳርኪንጃንግ ምጣኔ ሃብታዊ ዕድሎችን በመፍጠርና የማኅበረሰብ ውሳኔ አሳላፊነት እንዲጠነክር አስችሏል።

አጎት ባሪ “አሁን ሰዎች ተረድተዋል … በመሬት ይዞታ ረገድ ብልህና አስተዋዮች ነበርን” ሲሉ በምልሰታዊ ምልከታ አውስተዋል።

MA25133794-Vincent-Lingiari-1200w.jpg
Vincent Lingiari beside a plaque marking the handing over of the lease in Wattie Creek, 1975. Credit: National Museum Australia

ከአቦርጂናል የመሬት መብት ፊት ተጋርጠው ያሉ ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው?

የመሬት መብቶች ሂደት ውስብስብና ዘገምተኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ያለው ተመላሽ መሆን የሚችል ቀሪ መሬት ውስን ነው፤ የተወሰኑ የይገባኛል ጥያቄዎች የሕግ ወይም ፖለቲካዊ ጋሬጣዎች ይገጥሟቸዋል።

እኒህ ተግዳሮቶች ገርረው ቢኖሩም የመሬት መብቶች የአውስትራሊያን የወደፊት ብሔራዊ ዕርቅ፣ ፍትሕና የነባር ዜጎች የሉዓላዊነት እውቅና ፈር ላይ አስፈላጊ አካል ሆነው ይቆያሉ።

የነባር ዜጎች የመሬት መብቶች ለመላ አውስትራሊያውያን ፋይዳቸው ምንድን ነው?

ለአውስትራሊያ አዲስ ለሆኑቱ ስለ መሬት መብቶች ማወቅ ከእዚህች ሀገር ጥልቅ ታሪክ ጋር የመዋደጃ አንዱ መንገድ ነው። መሬትን ማጣት ሳይሆን፤ የዓለማችን በመሬትና ሰዎች መካከል ላለ ዘመናትን ላሸመገለ ተዋድዶ ዕውቅናንና ክብካቤን መቸር ነው።

ተዋድዶው ከ60,000 ዓመታት በላይ ፀንቶ ቆይቷል፤ ዛሬም ድረስ አለ።

Subscribe to or follow the Australia Explained podcast for more valuable information and tips about settling into your new life in Australia.   

Do you have any questions or topic ideas? Send us an email to australiaexplained@sbs.com.au 


Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now