Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

በእርግጥ ጃኑዋሪ 26 የሆነው ምንድን ነው?

Warga Pertama Australia mengadakan perarakan sempena Hari Australia

Meriki Onus dari suku kaum Gunai dan Gunditjmara mengambil bahagian dalam perarakan yang digelar Invasion Day Rally pada 26 Januari, 2025 di Melbourne, Australia. Hari Australia, yang dikenali sebelum ini sebagai Foundation Day, ialah sambutan tahunan rasmi setiap 26 Januari sempena ulangtahun ketibaan armada pertama di Sydney pada tahun 1788. Namun, kaum orang asli negara ini menganggap hari ini sebagai Hari Pencerobohan atau Invasion Day oleh pendatang kulit putih. Credit: Darrian Traynor/Getty Images Credit: Darrian Traynor/Getty Images

በአውስትራሊያ ታሪክ ውስጥ የከረሩ ክርክሮች ከሚካሔዱባቸው ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በአብዛኛው የሀገር ልደት ቀን ተብሎ ቢጠራም የይፋ የቅኝት ግዛት ምሥረታ ቀንንም ሆነ የጋራ ብልፅግናው ዕውን የሆነበትን ቀን አጣቃሽ አይደለም። ከቶውንም፤ በቅኝ ግዛት የተቀረፀ ፈርጀ ብዙ ታሪክን፣ ፖለቲካዊ ውሳኔዎችንና ያልተቋረጠ የነባር ዜጎችን መገዳደር ነፀብራቅ መሆን እንጂ። በእርግጥ ጃኑዋሪ 26 ምን እንደተከሰተ መገንዘቡ ቀኑ ስለምን በመላ ሀገሪቱ የተለያዩ ገፅታዎች እንደተላበሰ ገላጭ ይሆናል።


Published

Updated

By NITV

Presented by John-Paul Janke, Maram Ismail

Source: SBS



Share this with family and friends


በአውስትራሊያ ታሪክ ውስጥ የከረሩ ክርክሮች ከሚካሔዱባቸው ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በአብዛኛው የሀገር ልደት ቀን ተብሎ ቢጠራም የይፋ የቅኝት ግዛት ምሥረታ ቀንንም ሆነ የጋራ ብልፅግናው ዕውን የሆነበትን ቀን አጣቃሽ አይደለም። ከቶውንም፤ በቅኝ ግዛት የተቀረፀ ፈርጀ ብዙ ታሪክን፣ ፖለቲካዊ ውሳኔዎችንና ያልተቋረጠ የነባር ዜጎችን መገዳደር ነፀብራቅ መሆን እንጂ። በእርግጥ ጃኑዋሪ 26 ምን እንደተከሰተ መገንዘቡ ቀኑ ስለምን በመላ ሀገሪቱ የተለያዩ ገፅታዎች እንደተላበሰ ገላጭ ይሆናል።


አንኳሮች

  • የመጀመሪያዋ መርከብ ቦታኒ ቤይ መልሕቋን የጣለችው ጃኑዋሪ 18 ቀን 1788 እንጂ ጃኑዋሪ 26 አይደለም።
  • አውስትራሊያ በይፋ የቆመችው ፌብሪዋሪ 7 ቀን 1788 ነው፤ ጃኑዋሪ 26 ሳይሆን።
  • ጃኑዋሪ 26 ለነባር ዜጎች የተቃውሞ ነጥብና እውነት ነገራ ሆኖ የዘለቀ ነው።

ይህ መጣጥፍ መነሻውን ያደረገው የ SBS ብሔራዊ የነባር ዜጎች ጉዳዮች አዘጋጅ የNITV - The Point ተባባሪ አስተናጋጅ ጆን ፖል ጃንክ የቪዲዮ ዘገባ ተመርኩዞ ነው። ጃኑዋሪ 26 እንደምን የአውስትራሊያ ቀን ለመሆን እንደበቃና ስለምን በመላ ሀገሪቱ ሰዎች ዘንድ የተለያዩ ትርጓሜዎችን ይዞ እንደቀጠለ ከምንጩ ነቅሶ አመላክቷል።

አውስትራሊያ ውስጥ በጃኑዋሪ 26 ምን ተከሰተ?

ጃኑዋሪ 26 - 1788 ካፒቴን አርተር ፊሊፕ የእንግሊዝን ሰንደቅ ዓላማ ሲድኒ ኮቭ ላይ የሰቀለበት ቀን ነው። ሀገረ እንግሊዝን ከለቀቁ ከስምንት ወራት በኋላ በእዚያች ዕለት ምሽት የሙሉ ቅልፈቱ አሥራ አንዱም መርከቦች መልሕቃቸውን ፖርት ጃክሰን ላይ ጣሉ።

ምንም እንኳ ያ ወቅት ተዘውትሮ በሀገር ምሥረታ ዕለትነት ተደርጎ ቢሰበክም፤ እንግሊዞች ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉበት ሲልም በይፋ ቅኝ ግዛት የቆመበት አይደለም።

Sydney Cove, New South Wales, Australia, 1788, (1886).
Sydney Cove, New South Wales, Australia, 1788, (1886). Sydney Cove is a bay on the southern shore of Sydney Harbour. It was the site chosen in 1788 by Captain Arthur Phillip for the establishment of the first British colony in Australia, which later became the city of Sydney. The date of the colony's founding, 26 January, is today celebrated as Australia Day. Wood engraving from 'Picturesque Atlas of Australasia, Vol I', by Andrew Garran, illustrated under the supervision of Frederic B Schell, (Picturesque Atlas Publishing Co, 1886). (Photo by The Print Collector/Print Collector/Getty Images) Credit: Print Collector/Print Collector/Getty Images

የመጀመሪያው ቅልፈት ያረፈው ጃኑዋሪ 26 ነውን?

አይደለም። የመጀመሪያው ቅልፈት ቦታኒ ቤይ ያረፈው ጃኑዋሪ 18 ቀን 1788 ነው። ፊሊፕ፤ የአካባቢውን ለኑሮ አመቺነት ከገመገመ በኋላ፤ መሬቱ ለም ያልሆነና በቂ ንፁህ ውኃም ያለበት ስላልሆነ ለሠፈራ አመቺ አይደልም ሲል ከድምዳሜ ላይ ደረሰ።

የቅልፈቱ ጉዞ በብርቱ ንፋስ ሳቢያ ተስተጓጉሎ ዘገየ። ይህ በእንዲህ አንዳለም፤ ጃኑዋሪ 25 በካፒቴን ዤን ፍራንቼስ ዴ ላ ፐሩዝ የሚመሩ ሁለት መርከቦች መልሕቆቻቸውን ጥለው ታዩ። በማግሥቱ ጃኑዋሪ 26 ማለዳ ላይ ፊሊፕና አነስተኛ ቡድኑ ወደ ሲድኒ ኮቭ አመሩ። መለስተኛ ሥነ ሥርዓት አካሔዱ።

አውስትራሊያ መሠረቷ በይፋ የተጣለው መቼ ነው?

የአርተር ፊሊፕ አገዛዝ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ቅኝ ግዛትነትን በይፋ ጃኑዋሪ 7 ቀን 1788 በአዋጅ አስታወቀ።

የቅኝ ግዛቱ ወሰኖችም ከ135ኛ ሜሪዲያን አንስቶ ከአኅጉሪቷ ግማሽ አካል በላይ ወደ ምሥራቅ ተስፋፋ። ምንም እንኳ እውነታው ነባር ዜጎች ምድሪቱ ላይ ነዋሪ ሆነው ያሉ ቢሆንም፤ ወሰኖቹ የተዘረጉት የአውሮፓውያንን ውል መሠረት በማድረግ ነው።

Arthur Phillip, British naval commander, c 1789.
UNITED KINGDOM - JUNE 10: Engraving by W Sherwin after a painting by F Wheatly, of Phillip (1738-1814) who, in 1787, commanded the First Fleet carrying convicts to Australia. The day of his landing at Botany Bay, 26 January 1788, was later celebrated as Australia Day. Phillip founded a penal colony at Sydney Cove, Port Jackson, and was made Governor (colonial administrator) of New South Wales. (Photo by SSPL/Getty Images) Credit: Science & Society Picture Librar/SSPL via Getty Images

አስተራረፉ በነባር ዜጎች ላይ ተፅዕኖ ያሳደረው እንደምን ነው?

የመጀመሪያው ቅልፈት ያረፈበት ሥፍራ በመላው ሲድኒ ተፋሰስ 29 ያህል የነባር ዜጎች ጎሳዎች ባለቤትነት ስር ነበር። መሬቱ ሰው አልባ አልነበረም።

ለነባር ዜጎች ሰዎች ጃኑዋሪ 26 የመሬት ነጠቃ፣ አመፅና የእምቢኝ ባይነት መነሾን አውሺ ነው። ተፅዕኖው ዛሬም ድረስ ሰርፆ አለ።

ጃኑዋሪ 26 የአውስትራሊያ ቀን የሆነው ስለምን ነው?

ጃኑዋሪ 26 ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝባዊ ክብረ በዓልነት በጋዜጣ የታወጀው በአገረ ገዢ ላክላን ማኳየሪ በ1818 ነው። ያኔ ይታወቅ የነበረው እንደ የመጀመሪያ መልሕቅ መጣያ ቀን ወይም የምሥረታ ቀን ነበር።

በ1888 አብዛኛዎቹ ቅኝ ግዛቶች ጃንዋሪ 26ን የምሥረታ ቀን ወይም የክብረ በዓል ቀን በማለት ማክበር ጀመሩ፤ እንዲያም ሆኖ ግና ቅኝ ግዛቶቹ በተናጠል የየራሳቸው የሆኑ የምሥረታ ቀኖች የሚሏቸው ነበሯቸው።

በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ግድም፤ የአውስትራሊያ ሀገር በቀሎች ማኅበር ጃኑዋሪ 26 ብሔራዊ ክብረ በዓል እንዲሆን ብርቱ ጎትጓች ሆነ። ማኅበሩ ፌዴሬሽንን አስተዋወቀ፤ ግና አባልነትን ለነጭ አውስትራሊያ ተወላጅ ወንዶች ብቻ የተገደበ አደረገ።

የአውስትራሊያ ቀን ፌዴሬሽንን አውሺ ነው?

አይደለም። የአውስትራሊያ የጋራ ብልፅግና ዕውን የሆነው በዕለተ አዲስ ዓመት 1901 ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የፌዴራል ፓርላማ የተሰየመው ሜይ 9 ቀን 1901 ነው።

ጃኑዋሪ 26 አንዳቸውንም ኩነቶች አውሺ አይደለም። አውሺነቱ የ1788ቱን የሲድኒ ኮቭ አስተራርፍን እንጂ።

የአውስትራሊያ ቀን ስያሜን መጠቀም የተጀመረው መቼ ነው?

ብሔራዊ የአውስትራሊያ ቀን ዕሳቤ ብቅ ያለው ለመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ገንዘብ የማሰባሰቢያ ጥረት አካል በመሆን ነው። ለበርካታ ዓመታትም ኩነቶቹ የተካሔዱት ጁላይ ላይ ሳይሆን ጃኑዋሪ ላይ ነበር።

በ1918 የተወሰኑ ድርጅቶች ጃኑዋሪ 26ን የአውስትራሊያ ቀን በማለት መጥራት ጀመሩ። በ1930 የአውስትራሊያ ሀገር በቀሎች ማኅበር ለስያሜው በይፋ ይሁንታን ቸረ። በ1935 በርካታዎቹ ክፍለ ሃገራት የስያሜውን ፈለግ ተከተሉ። ኒው ሳውዝ ዌይልስ ግና ለበርካታ ዓመታት የክብረ በዓል ቀን በሚል መጥራቱን ቀጠለ።

ጃኑዋሪ 26 ለነባር ዜጎች የሐዘን ቀን የሆነው ስለምን ነው?

በ1935 መልሕቅ የተጣለበት 150ኛው መታሰቢያ ዕለት፤ የነባር ዜጎች መሪዎች የሐዘን ቀን አደራጁ። ኢፍትሐዊነት፣ አግላይነትና መሬት ነጠቃ ትኩረት እንዲያገኝ ጥሪ የተካሔደበት አንዱ ቀዳሚው ብሔራዊ የአቦርጂናል ሲቪል መብቶች ተቃውሞ ወቅት ነበር።

ከዚያን ጊዜ አንስቶም፤ ጃኑዋሪ 26 ለአያሌ የነባር ዜጎች ማኅበረሰባት ብርቱ የተቃውሞ፣ ዝክርና ተገዳዳሪነት ቀን ሆኖ አለ።

ጃኑዋሪ 26 መቼ ነው ብሔራዊ ሕዝባዊ ክብረ በዓል ቀን የሆነው?

ሕዝባዊ የክብረ በዓል ቀንነቱ አደላደል ለአሠርት ዓመታት ያህል በክፍለ ሃገራት መካክል የተለያየ ነበር። የተወሰኑቱ በዕለትቱ ጃኑዋሪ 26ን ሲያከብሩ፤ ሌሎች የሕዝባዊ በዓል ቀንነቱን በቀጣዩ ሰኞ ያደርጉ ነበር።

ከ1988 ሁለተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ሁሉም ክፍለ ሃገራት ቀስ በቀስ የሕዝባዊ በዓል ቀኑን አንድ ላይ ማድረግ ጀመሩ። በ1994 ጃኑዋሪ 26 ወጥ ብሔራዊ ሕዝባዊ የክብረ በዓል ለመሆን በቃ።

Australia Day Live 2024
SYDNEY, AUSTRALIA - JANUARY 26: A general view is seen during Australia Day Live 2024 at the Sydney Opera House on January 26, 2024 in Sydney, Australia. (Photo by Don Arnold/WireImage) Credit: Don Arnold/WireImage

ጃኑዋሪ 26 አሁንም ድረስ ፋይዳ ያለው ስለምን ነው?

ጃኑዋሪ 26 ዘርፈ ብዙ ትርጓሜዎችን ይዞ አለ። ለተወሰኑቱ፤ ብሔራዊ ማንነትንና ክብረ በዓልን ይወክላል። ለበርካታ ነባር ዜጎች የወረራ፣ ዕጦትና እምቢኝ ባይነት ተምሳሌነትን ይዟል።

በመላ አውስትራሊያ ውይይቶቹ ቀጥለው ሳለ፤ የዕለቱን ሙሉዕ ታሪክ መገንዘቡ ለእውነት ነገራና ይበልጥ ግንዛቤን የጨበጠና አካታች መፃኢ ጊዜን ለመገንባት ማዕከል ነው።

ይህ የአውስትራሊያ ስትገለጥ ታሪክ የተዘጋጀው ከNITV ጋር በመተባበር ነው። ኦዲዮ ከጆን ፖል ጃንክ የNITV አስረጅ ቪዲዮ ቅንጭብ ነው።


Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now