Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ ከመድረክ ወደ ቴሌቪዥን ድራማ

Community
Actress Senayt Mebrahtu. Source: Bob Mcgahan / Carolina Häggström

ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ከውልደት ቀዬዋ ተንስታ፣ የካርቱም የስደት ሕይወቷን አጣቅሳ፣ የአውስትራሊያ የሠፈራና ምዕራባዊ የሥነ ጥበብ ሕይወት ጅማሮዋን አውግታለች። በቀጣይነትም እንደ ፅጌረዳ አበባ ውበትና እሾህን በተላበሰው የጥበብ ሕይወት ጉዞዋ ውስጥ የተፈተነችባቸውን ተግዳሮቶችና በሐሴት የተመላችባቸውን ስኬቶች ታነሳለች።


Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS



Share this with family and friends


ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ከውልደት ቀዬዋ ተንስታ፣ የካርቱም የስደት ሕይወቷን አጣቅሳ፣ የአውስትራሊያ የሠፈራና ምዕራባዊ የሥነ ጥበብ ሕይወት ጅማሮዋን አውግታለች። በቀጣይነትም እንደ ፅጌረዳ አበባ ውበትና እሾህን በተላበሰው የጥበብ ሕይወት ጉዞዋ ውስጥ የተፈተነችባቸውን ተግዳሮቶችና በሐሴት የተመላችባቸውን ስኬቶች ታነሳለች።


በነጮች ዓለም የጥቁር ገፀ ባሕሪይን ተላብሶ የመተወን አጋጣሚ ውስን ነው።

ለምን? ቢሉ አንድም የተውኔት ሕይወቱ ምንጭ ገፀ ባሕሪያት የሚቀዱት ከአገሬው ነው፤ ሲልም በነጭ የብዕር ቀለም የጥቁር ዓለምን ነቅሶ የገሃዱን ዓለም ስጋ ማላበስና ነፍስ መዝራት አዋኪ ነውና።

ደግነቱ ግና የሰናይት የጥበብ እስትንፋስ የተመላው በጥበብ ፍቅር እንጂ በዝና ፍለጋ ባለመሆኑ በተግዳሮት ፊት ስኬትን አሳቢ አድርጓታል።

የማኅበረሰቧን መሠረት ባለመልቀቋና ተነጥላም ተንሳፋፊ ባለመሆኗ የአቢሲኒያ ዳንስ ቡድን መሥራች፣ ድምፃዊትና ተወዛዋዥ ሆና ባሕላዊ ዝንቅነትን ለአገረ አውስትራሊያ እነሆኝ አለች።

በተለያዩ ፌስቲቫሎች ላይ ባሕላዊ ሙዚቃና ውዝዋዜዎችን ለመድረክ አብቅታለች።

ሰናይት በአቢሲኒያ የዳንስ ቡድን አልተወሰነችም።

ዘልቃ አንድ ሙዚቃዊ የቲአትር ቡድን ከሌሎች አፍሪካውያን የጥበብ ሰዎች ጋር ተቧድና መሠረተች።

Community
Source: Abyssinian Dance Group

የቲአትር ኩባንያና የመድብለ ባሕል ድርጅቶችም "አለን" ብለው ተቀላቀሉ። 

በጋራ "i am here" የሚል የአዲስ ሠፋሪዎችን ሕይወት የሚያንፀባርቅ ሙዚቃዊ ድራማ ለመድረክ አበቁ።

Community
Actress Senayt Mebrahtu (C). Source: S.Mebrhatu

የአገሬውን ሰው ጨምሮ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ አባላትም ታዳሚዎች ሆኑ።

ስኬት ስኬትን ወለደ።

ከመድረክ ትወና ወደ ቴሌቪዥን ድራማ

የሰናይት የሥነ ጥበብ ኮከብ ከመድረክ ወደ ቴሌቪዥን ድራማ ብርሃኑን ፈነጠቀ።

እ.አ.አ.  ከ2010 አንስታ "Terra Nova" ተከታታይ የቴሌቪዥን ሳይንሳዊ ድራማ ላይ ለረጅም ጊዜ ተሳታፊ ሆነች።

Community
Actress Senayt Mebrhatu. Source: Carolina Häggström

በተጓዳኝም ሌሎች በርካታ ትወናዎችን እየከወነች ቀጠለች።

ትልቁ የ2022 ሥራዋ ግና የ "Elvis" ሙዚቃዊ ድራማ ትወናዋ ነው።  

 


Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now