አንኳሮች
- ትሩፋቶች
- ፋይዳዎች
- የአገልግሎት ጉዞ
የማኅበሩ አንዱ ትልቁ ውለታ ሳይከስም ይህን ያህል ጊዜ መሔዱና በርካታ ሥራዎችን መሥራቱ ነው፤ ማኅበሩ በማደግ ላይ ሳይሆን ባለበት እያዘገመ ነው ያለው።ደራሲ አዳሙ ተፈራ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት
የማኅበሩ ጥቅምና ጉዳቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰበትም ጊዜ ነበር፤ እንደ አመሠራረቱ ብዙም ደረጃ ላይ አልደረሰም። በጣም የተለየ ሥራ ሠርቷል ብዬ የማስበው 23 ገፆች ያሉት መተዳደሪያ ደንብ ማፅደቁ ነው።አቶ ዓለማየሁ በዛብህ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ
ወደ ላይ ጥሩ ቦታ ደርሰን፤ ወደ ታች የወረድንበት ሁኔታ አለ።አቶ አሕመድ ዳውድ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ሥራ አስፈፃሚና ቦርድ አባል
የማኅበሩ ድክመት እንዳለ ሆኖ፤ የኢትዮጵያዊነት ወግና ባሕልን በመጠበቅ፣ በስፖርት፣ የአዲስ ዓመትንና ሌሎችንም ሥራዎች ሲሠራ የቆየ ነው።ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ የቀድሞው በታዝማኒያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤
ችግሮች እንዳሉ ይታወቃል። የጎላ እንቅስቃሴ ባይኖረውም፤ ማኅበሩ ጠፍቷል፤ የለም ማለት አይቻልም። አንድ ማኅበረሰብ የሚጠናከረው አመራርና ፖሊስ ሲኖረውና ያንንም ተንተርሶ ሲሠራ ነው። በእርግጥ ማኅበሩ ያንን ተንተርሶ እየሠራ ነው ወይ?ዶ/ር ቢቾክ ዋን፤ በቪክቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ መምህር