ኢመረተስ ፕሮፌሰር ባየ ይማም፤ በአዲስ አበባና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች የቋንቋ መምህር፤ በቅርቡ ለአንባቢያን እነሆኝ ባሉት "የአማርኛ ሰዋሰው" መጽሐፋቸው አማርኛ ግዕዝንና አገውኛን ተክቶ እንደምን ለቤተ መንግሥት ቋንቋነት እንደበቃ፤ የቋንቋን ውልደትና ሞት ጊዜ ፈጂነት ከሌሎች አንኳር ሃሳቦቻቸው ጋር አያይዘው ይናገራሉ።
አንኳሮች
- ቋንቋና ማንነት
- የአማርኛ ቋንቋ ጅማሮና ለብሔራዊ ቋንቋነት መብቃት
- የሰዋሰው ትምህርት ዋነኛ ዓላማ
ሃሳብ፣ ስሜትና ልዩ ድምፀት ተዋሕደው ነው ወደ ሰሚ ጆሮ የሚደርሱት።ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም
አማርኛ ግዕዝና አገውኛን ተከቶ፤ ከተራ ሕዝባዊ ጠቀሜታ የቤተ መንግሥት ቋንቋ መሆን የጀመረው በ12ኛው ክፍለ ዘመን ነው።ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም
ቋንቋ ውልደቱም፤ ሞቱም ጊዜ ፈጂ ነው።ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም
Share





