በሚዲያ የነባር ዜጎች ውክልና፤ ምን ዓይነት ለውጥ እየተካሔደ ነው፤ ፋይዳውስ ምንድን ነው?

FIRST NATIONS MEDIA REPRESENTATION HEADER ALC.png

የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የሚዲያ ውክልና ታሪካዊ ተሞክሮው በጅምላ ፍረጃና መገለል የተቀነበበ ነው፤ ምንም እንኳ እያዘገመ በመለወጥ ላይ ያለም ቢሆን። እንደ ብሔራዊ የነባር ዜጎች ቴሌቪዥን (NITV) እና ማኅበራዊ ሚዲያ ያሉ መድረኮች ጋሬጣዎችን በጎን አልፈው፤ የነባር ዜጎችን ድምፆች እያሰሙና የአውስትራሊያን ዝንቅ ባሕላዊ ማንነት በላቀ አካታችነት እየታደጉ ይገኛሉ። ስለ እኒህ ለውጦች፤ የሀገሪቱን እውነተኛ ታሪክ ፣ ያልተቋረጠ የፍትሕ ፍለጋ ጉዞና የበለፀገው ባሕል እንደምን ለዘመናይቱ አውስትራሊያ መሠረት እንደሆነ ጥልቅ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ጋባዥ ነው። የነባር ዜጎችን አተያዮች መረዳት ከበሬታን ወደ ተላበሰና የጋራ ጉድኝትን ወደ አቆራኘ ጠቃሚ እርምጃ አምሪ ነው።


አንኳሮች
  • የአውስትራሊያ ሚዲያ የነባር ዜጎች ድምፆችን በማግለል፤ አተያዮቻቸው ያልታከሉባቸውን አመለካከቶች የሕዝብን ዕይታ በጅምላ ምልከታ ለመቅረፅ ታሪካዊ ተሞክሮ አለው
  • የነባር ዜጎች ሚዲያ ድምፆችን ለስሚ ያበቃሉ፣ ባሕል ተጠብቆ እንዲቆይ ያደርጋሉ፣ እንዲሁም፤ የጅምላ ፍረጃን ይገዳደራሉ
  • እንደ ቲክቶክና ኢንስታግራም ያሉ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ታሪክ ነገራን ያጎላሉ
በተለምዶ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች በሚዲያ የሚገለጡት በእጅጉ በተሳሳተ መልኩ ነው። ቀደም ባሉ ጋዜጦች፣ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ነባር ዜጎችን በአብዛኛው በእጅጉ ዝቅ አድርገውና አዛንፈው የሕዝብን ዕይታ ቀርፀዋል።

በእናታቸው ወገን ኩሩ ኑንጋር ያማትጂ ናጉጃ ኑንዳ እና በአባታቸው ወገን ያውሩ ጊጃና ጉንያንዲ ሴት ሊያን ጂላዲ ዶልቢ "እኔ ወጣት ሳለሁ፤ የእኛ ሰዎች የሚዲያ ውክልና እምብዛም አልነበረም። አሁን ግና መሰናክሎችን እያለፍንና በጥቁር ልህቀት ሐሴትን እየተላበስን ነው። የነባር ዜጎች ድምፆች በዓለም አቀፍ ደረጃ መሰማት ድንቅ ነገር ነው" ይላሉ።

የነባር ዜጎች ሚዲያ አውስትራሊያ ተባባሪ መሥራች፣ የነባር ዜጎች ቴሌቪዥን፤ የንግድ፣ መለያና ዲጂታል ዋና ኃላፊና የካቢ ካቢ፤ ጎሬንግ ጎሬንግ ሰው አዳም ማኖቪች፤ የነባር ዜጎች ዲጂታል ሁሉን አቀፍ አማካሪ ቡድን አባል፤ የረጅም ጊዜያት አሉታዊ ገፅታ ቅቡ መዘዞችን እንዳስከተለ ሲያመላክቱ፤

"ከ1990ዎቹ መጀመሪያ አንስቶ፤ ብዙኅን መገናኛ፤ ጋዜጦችና ሬዲዮ በሰዎች የነገሮች ምልከታ ላይ መጠነ ሰፊ ተፅዕኖ አሳድረዋል። ነባር ዜጎች ባልሆኑቱ አውስትራሊያውያን ዘንድ ነባር ዜጎች እንደምን እንደሚታዩ ምልከታዎችን ቀርጿል፤ በአብዛኛውም ሐሰት ላይ የተመረኮዙ አሉታዊ የጅምላ አተያዮች በሆነ መልኩ" በማለት አስረድተዋል።

የቅርብ ጥናቶች እንዳመላከቱት ማኅበረሰባቸውን አስመልክቶ የብዙኅን መገናኛ ሚዛናዊ አተያዮችን ያዘግባሉ የሚል አመኔታ ያላቸው ነባር አውስትራሊያውያን ዘጠኝ በመቶ ብቻ ናቸው።
First Nations media rep.png
Left: Tanja Hirvonen. Centre: Adam Manovic. Right: Leanne Djilandi Dolby ( Credit: SBS)

መዋቅራዊ ጋሬጣዎች ምንድን ናቸው?

ምንም እንኳ መሻሻሎች ቢታዩም፤ መዋቅራዊ ጋሬጣዎች እንደ የነባር ዜጎች ሚዲያ አውስትራሊያ ላሉ ነባር ዜጎች መር የሚዲያ ድርጅቶች መዋቅራዊ ጋሬጣዎች አሁን ድረስ ተደቅነው አሉ። እምብዛም ድጎማና ጊዜ ያለፈባቸው መሠረተ ልማቶች ተደራሽነታቸውን ገድበው አሉ።

ይሁንና፤ ዋነኛ የብዙኅን መገናኛ ከአሉታዊ የጅምላ አተያዮች ራቅ ቢሉም፤ ጥልቅ ባሕላዊ ጭብጦችን ወይም ተዓማኒ የሆኑ የነባር ዜጎች ድምፆችን ለማካተት ሳይበቁ ቀርተዋል።

አዳም ማኖቪች፤ እኒህን ተግዳሮትች ለመወጣት፤ ነባር ዜጎች የራሳቸው ትርክቶች ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል ቁልፍ ጉዳይ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተውታል።

የነባር ዜጎች ሚዲያ ሚና

እንደ FNMA እና NITV የመሳሰሉ የነባር ዜጎች መድረኮች ትርክቶችን መልሶ የራስ ለማድረግና የጅምላ አተያዮችን ለመገዳደር ወሳኝ ናቸው። FNMA በመላ አውስትራሊያ ከ500 በላይ ለሆኑ ሠራተኞች ድጋፍን የሚቸር ሲሆን፤ እንዲሁም፤ ነባር ዜጎች ወደ ሚዲያ ኢንዱስትሪ ዘልቀው እንዲገቡ ለማስቻል ስልጠናዎችን ይሰጣል።

NITV ሕልውናውን ተላብሶ ስርጭቱን ለአየር ያበቃው በ2007 ሲሆን፤ ከ2012 አንስቶ የSBS አካል የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ተዓማኒ ታሪክ ነገራ መድረክ በመሆን እያገለገለ ነው።

አዳም ማኖቪች መንግሥት የነባር ዜጎች ብሔራዊ ስርጭት ድንጋጌ መሠረት ለእነዚህ ተደራሽነቶች ዘላቂ ድጎማ እንዲያደርግ ጉትጎታ ያደርጋሉ።

"የነባር ዜጎች ሚዲያ ማኅደርን ጠብቆ ማቆየት ሁነኛ ጉዳይ ነው፤ ስለምን ለመጪው ትውልድ ቋንቋና ባሕል ጠብቆ ለማቆየት ያበቃልና። እኒህ ቀረፃዎች እንዳይጠፉ እርግጠኞች መሆን እንፈልጋለን። ከእኛ ማንነት ጋር የተቆራኙ ናቸውና" ይላሉ።

መድረኮቹ የጅምላ አተያዮችን የሚገዳደሩ፣ ባሕላዊ ኩራትን የሚታደጉና የነባር ዜጎችን እውነታዎች የሚያንፀባርቁ፣ ተዓማኒ ታሪክ ነገራን የሚያቀርቡ ናቸው።
NITV Muy Ngulayg
First Nations hub of inner knowledge, traditional culture and lore.

የሚዲያ ውክልና ማነስ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሰው እንደምን ነው?

የሚዲያ ውክልና ማንነትን በመቅረፅና የአውስትራሊያ ነባር ዜጎችን በራስ የመተማመን ውስጣዊ ስሜትን በመገንባት በእጅጉ የጎላ ሚና ይጫወታል። ታሪካዊ ተሞክሮው ግና፤ ጎጂ አሉታዊ የጅምላ ፍረጃንና መዋቅራዊ ዘረኝነትን ማፅናት ነው።

የጃሩና ባኑባ ሴት፣ የክሊኒካዊ ስነ ልቦና ተጠባቢና የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የስነልቦና ባለ ሙያዎች ማኅበር የቦርድ አባል ታንጃ ሂርቮነን እንዲያ ያሉ ትርክቶች በተለይም አዋኪ በሆኑ ወቅቶች እንደምን ጥልቅ ሁከትን እንደሚያሳድሩ ሲያስረዱ፤

"ሚዲያ ጎጂ የሆኑ የጅምላ ፍረጃዎችን ያለማቋረጥ ወይም ከእውነታ የራቁ ይዘቶችን ሲያሰራጭ፤ ዘረኝነትንና አግላይነትን መጠነ ሰፊ በሆነ ሁኔታ ያፀናል። ከወዲሁ ውስጣዊ የስሜት ትግል ላይ ያሉ፤ እኒህን ትርክቶች ሲያዩ በእጅጉ ለሁከት ይዳረጋሉ" ይላሉ።

ይሁንና፤ አዎንታዊ የሚዲያ ውክልና ግና መጠነ ሰፊ ትሩፋቶችን ይቸራል። ጥናቶች እንዳመላከቱት፤ ሁሉን አቀፍና ተዓማኒነትን የተላበሱ የነባር ዜጎች ገፅታዎች ባሕላዊ ኩራትን ይታደጋሉ፣ ማኅበረሰባዊ ተግባቦትን ያጠናክራሉ፣ የሕይወት ስኬትንም ያሻሽላሉ።

ለአብነትም፤ የብሔራዊ ስምምነት ክፍተትን በማጥበብ የነባር ዜጎች የሚድያ ድርሻ ዘረኝነትን ለመቀነስና ተደራሽ መረጃን ተመርኩዞ ከውሳኔ ላይ ለመድረስ ያለው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን አመላክቷል።

አዎንታዊ ውክልናም እንዲሁ፤ በውል ግንዛቤን ያልጨበጠ ዘገባ አቀራረብን ለመገዳደር ያግዛል። የነባር ዜጎች ድምፆች እንደ NITV ወይም ማኅበራዊ ሚዲያ ባሉ መድረኮች በታሪክ ነገራ ሲካተቱ፤ ግንዛቤን ያዳብራል ነባር ዜጎች ባልሆኑ አውስትራሊያውያን ዘንድም ከበሬታን ያስገኛል።

ይህ ዓይነቱ ለውጥ ለዕርቅ ጥረቶች እጅግ ከፍ ያለ ድጋፍን ያበረክታል።

የማኅበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪ እና የባዮኬሚካል ተማሪ የሆነችው ጂላንዲ ዶልቢ፤ ራስን በሚዲያ የመመልከት የሚያሳድረውን ተጓዳኝ የእኔነት ውክልና ስሜትን አፅንዖት ሰጥታ ስትናገር፤

"እንደ አቦርጅናል ሰው በበቂ መልኩ የራስን ውክልና ማየት አለመቻል፤ የመገለል ስሜትን ያሳድራል። ውክልና ማለት እኔን የመሰሉ ተመሳሳይ ግቦችና ጥንካሬ ያላቸው ሰዎች መኖራቸውን ማወቅ ነው" ብላለች።

ተዓማኒነት ላላቸው ታሪክ ነገራዎች ቅድሚያ በመስጠትና የነባር ዜጎች ድምፆችን ኃይል በማላበስ ረገድ ሚዲያ ያለፈን ቁስል እንዲያጠገግ ከማድረግ አልፎ ሁሉን አቀፍ መፃዒ ጊዜን ለሁሉም አውስትራሊያውያን የመገንባት አቅም አለው።

ታንጃ ሂርቮነንም በፊናቸው "የእኛ [የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች] ጥንካሬ መሠረቱ ባሕላዊ ፅንዓታችን ነው። ልማዶቻችንን፣ ቋንቋና ታሪኮቻችንን በሚዲያ አማካይነት ትድግናን በማላበስ፤ የአሉታዊ ጎጂ ትርክቶችን ተፅዕኖዎች መቋቋም እንችላለን" ብለዋል።
Young Australian  woman looking at a phone
Social media has proven to have the power that enables First Nations people to challenge misinformation. Credit: davidf/Getty Images

ማኅበራዊ ሚዲያ ለለውጥ መሳሪያነት

ማኅበራዊ ሚዲያ ለአውስትራሊያ ነባር ዜጎች በመሸጋገሪያ መድረክነት ብቅ ብሎላቸዋል። እንደ ቲክቶክ፣ ኢንስታግራምና ፌስቡክን የመሳሰሉ መድረኮች የተለምዶ ሚድያን በጎን በማለፍ ታሪኮቻቸውን በቀጥታ ለሉሏዊ ታዳሚዎች ለማጋራት አስችሏቸዋል።

ይህ አቅም ነባር ዜጎች፤ በአንድ በኩል ባሕላዊ ልውውጥን እያደረጉ በሌላ በኩል የተሳሳተ መረጃን ለመገዳደር እንዲበቁ አድርጓቸዋል።

እንደ #IndigenousX ያሉ ሃሽታጎች የማንቂያና የትምህርት ማዕከል ሆነዋል።

አዳም ማኖቪች "የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ይመጣሉ፤ ይሄዳሉ። ይሁንና እስከ መቼውም የማይለወጠው ግና የእኛ ታሪኮችን የመተረክ ክህሎት ነው። ቲክቶክ፣ ፊልም፣ ሬዲዮ ወይም የሕትመት ውጤት ይሁኑ፤ እኒህን መድረኮች ለእኛ ጠቀሜታ ባለው መልኩ ባሕላችንን ለማሳየት፤ እንደምን መጠቀም እንዳለብን እናውቃለን" ሲሉ አስረድተዋል።

መጪው ጊዜ ምንን ይዟል?

ውክልናን ለማጎልበት በመላ ዋነኛና ማኅበረሰብ መር በሆኑ የሚዲያ መስኮች ሥርዓታዊ ለውጥን መተግበር ግድ ይላል። ይህም ማለት ለነባር ዜጎች ድምፆች ቦታን መስጠት ብቻ ሳይሆን፤ እንደምን ታሪኮች እንደሚመረጡ፣ እንደሚነገሩና እንደሚጋሩ አስቻይ የሆነ ዘለቄታ ያለው ድጋፍን ማድረግንም ማካተትን ያክላል።

አዳም ማኖቪች፤ የነባር ዜጎች የብዙኅን መገናኛ ድንጋጌ የመሰለው እንደ SNMA እና NITV ለመሳሰሉቱ መድረኮች አስተማማኝ ድጎማ እንዲያገኙ እንዲያስደርግ ጥሪ ያቀርባሉ።

ታንጃ ሂርቮነንም በፊናቸው፤ በዋነኛ ሚዲያ ተቋማት ባሕላዊ ጥንቃቄ እንዲተገበርባቸው፤ ሲልም፤ ፍትሐዊ የሆነ ገፅታዎች እንዲንፀባረቁባቸው በእያንዳንዱ ዘርፍ የነባር ዜጎች ድምፆች ተሳትፎ መኖር እንደሚገባው ያመላክታሉ።

ሊያን ጂላንዲ ዶልቢም፤ በሁሉም የሚዲያ ዘርፎች የነባር ዜጎች ስኬቶች ድምቀት እንዲያገኙ ስታበረታታ፤

"የሰዎቻችንን ታሪኮች በፊልም ይሁን ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ መመድረኮች ለማጋራት ተጨማሪ ዕድሎችን እንሻለን፤ እንዲሁም በፈጠራ እንዲስትሪዎች ውስጥ ለመዝለቅ ተጨማሪ ድጋፍ እንፈልጋለን" ብላለች።

የአውስትራሊያ ነባር ዜጎችን ገፅታዎች በሚዲያ ውስጥ ማስረፁ እየተካሔደ ነው፤ ሆኖም ገና ጅማሮ ላይ ያለ ሆኖ ነው ያለው። እንደ NITV እና ማኅበራዊ ሚዲያ ያሉ መድረኮች ለተዓማኒ ታሪክ ነገራ ተስፋን እየቸሩ ሲሆን፤ ዋነኛ የሚዲያ ተቋማት የአውስትራሊያን የበለፀገ ብዝኅነት ለማንፀባረቅ ከይስሙላ ማዶ መሻገር ይኖርባቸዋል።

የነባር ዜጎችን ድምፆች ለልቀት ማብቃት በማኅበረሰባት ዘንድ ግንዛቤን ከማዳበርም ዐልፎ የአውስትራሊያን ባሕላዊ መስኮች ያበልፅጋል። አዳም ማኖቪች እንዳሉት፤ የነባር አውስትራሊያውያን ዜጎች የሚዲያና ባሕላዊ አዎንታዊ አስተዋፅዖዎች “ውዳሴያዊ ትሩፋቱ ለሁሉም” ነው።
Subscribe to or follow the Australia Explained podcast for more valuable information and tips about settling into your new life in Australia.   

Do you have any questions or topic ideas? Send us an email to australiaexplained@sbs.com.au.

Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service