Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

"ትዝታ ትናንትን በምልስት በማውሳት ዛሬ ላይ ሕይወት ዘርተን የምናቆየው ነው፤ ለፊልሜ መጠሪያ ያደረግኩትም ቃለ መልዕክቱ ለልብና ለነፍስ ስለሆነ ነው"አራማዝት ካላይጂያን

TP.png
TEZETA (L), Tezeta's documentary film Director Aramazt Kalayjian (C), interior of St George church in Addis Ababa (R). Credit: Armenian Film Festival and R.P. Sevadjian

የ"ትዝታ" ዘጋቢ ፊልም ዳይሬክተር አራማዝት ካላይጂያን፤ አርመንያውያን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዓለም ውስጥ ከሠልፈኛ ባንድ ምሥረታ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ቀማሪነትና የዘመናዊ ሙዚቃ ጉልህ የጥበብ አሻራዎቻቸውን ስለሚዘክረው ፊልማቸው ጭብጦች ያወጋሉ። አርመናውያን በአጼዎቹ ዮሐንስ አራተኛ፣ ዳግማዊ ምኒልክና ቀዳማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥታት ውስጥ ከአድዋ ጦርነት ጣሊያንን መመከቻ መሣሪያ አበርካችነት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ግንባታዎችና በሌሎችም ዘርፈ ብዙ መስኮች ያበረከቷቸውን ሁነኛ አስተዋፅዖዎች ያነሳሉ። ትዝታ ነሐሴ 25 /ኦገስት 31 በሜልበርን Lido Cinemas ለሕዝብ ይቀርባል።

Published

Updated

By Kassahun Negewo

Source: SBS

Share this with family and friends

የ"ትዝታ" ዘጋቢ ፊልም ዳይሬክተር አራማዝት ካላይጂያን፤ አርመንያውያን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዓለም ውስጥ ከሠልፈኛ ባንድ ምሥረታ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ቀማሪነትና የዘመናዊ ሙዚቃ ጉልህ የጥበብ አሻራዎቻቸውን ስለሚዘክረው ፊልማቸው ጭብጦች ያወጋሉ። አርመናውያን በአጼዎቹ ዮሐንስ አራተኛ፣ ዳግማዊ ምኒልክና ቀዳማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥታት ውስጥ ከአድዋ ጦርነት ጣሊያንን መመከቻ መሣሪያ አበርካችነት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ግንባታዎችና በሌሎችም ዘርፈ ብዙ መስኮች ያበረከቷቸውን ሁነኛ አስተዋፅዖዎች ያነሳሉ። ትዝታ ነሐሴ 25 /ኦገስት 31 በሜልበርን Lido Cinemas ለሕዝብ ይቀርባል።

አንኳሮች

  • ስደትና ሠፈራ
  • 40ዎቹ ልጆች
  • የአርመንና ኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ስምሙነት
  • ማንነት፣ ባሕልና ቋንቋ
  • ትዝታ

Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now